የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ  

91

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 18/2016 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ  ጀምሯል።

ለአንድ ቀን በሚቆየው ጉባኤ ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት የስነ ምግባር ደንብ እና የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት አዋጅ ላይ በመምከር ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የሰው ተኮር የልማት ስራዎች፣ የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ ተቋማዊ ግንባታና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት በከተማ አስተዳደሩ በዘጠኝ ወራትና ሌሎች  የተከናወኑ  ስራዎች ይዳሰሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም