ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተቀብለው አነጋገሩ

113

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2016(ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸውን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

የቢል እና ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ስርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ እንዳለው ገልጸዋል።

ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሰራለንም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም