ለአውቶብስ ብቻ የተለዩ መንገዶች የብዙኀን ትራንስፖርትንት የምልልስ አቅም በማሳደግ ፍሰቱን ያሳልጣሉ

83

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2016(ኢዜአ)፡- ለአውቶብስ ብቻ የተለዩ መንገዶች የብዙኀን ትራንስፖርትን  የምልልስ አቅም በማሳደግ  የትራንስፖርት  ፍሰቱን  እንደሚያሳልጡ  የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ ።

 በየጊዜው የሚጨምረው የከተማዋ ነዋሪዎች ቁጥር ካለው የትራንስፖርት አማራጭ እና ብዛት ጋር አለመጣጣሙ ይጠቀሳል።

የከተማ አስተዳደሩ የትራፊክ መጨናነቅና የትራንስፖርት እጥረቱን ለማቃለል የሚረዱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።


 

ከነዚህ መካከል በአንዳንድ መንገዶች በስተቀኝ በኩል ከነባሮቹ አውቶብስ ማቆሚያዎች በተጨማሪ ለአውቶብስ ብቻ የሚሉ ጹሑፎች በጎልህ ተጽፈው ይታያል።

ለአውቶብስ ብቻ የተለዩ መንገዶችን በተመለከተ  ኢዜአ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ምትኩ አስማረ ጋር ቆይታ አድርጓል።

በከተማው ውስጥ ያለው የአውቶብስ ቁጥር ከአገልግሎት ፈላጊው ጋር ያለመመጣጠን እንዲሁም የተሳፋሪ ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መምጣት ችግሩን እንዳጎላው ተናግረዋል።

ለአውቶብስ ብቻ የተለዩት መንገዶች የአውቶብሶችን ምልልስ በማቀላጠፍና ተሳፋሪዎችን በፍጥነት እንዲጭኑ በማድረግ ፍላጎትና አቅርቦቱን ለማመጣጠን ይረዳሉ ነው ያሉት።

ለአውቶብስ ብቻ የተለዩ ቦታዎችን በመጠቀም በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ የአውቶብሶችን የምልልስ አቅም በመጨመር ችግሩን ለማቃለል እየሰራን ነው ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል።

ከዊንጌት እስከ ጊዮርጊስ ለአውቶብስ ብቻ የተለዩና ቀደም ብለው የተጀመሩ ስራዎችን በቀጣይ ወደ ጀሞ ሶስት እንደሚሰፋ ገልጸዋል፡፡

መስመሮቹን ማሳደግ በራሱ የትራፊክ መጨናነቁን እንደሚያቃልልና በተጠቀሱት ቦታዎች ያለአግባብ በሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ የቁጥጥር ስራዎች በተጠናከረ መንገድ ይሰራል ብለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም