ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
መንግስት ከሚመሰርተው ፓርቲ ጋር ተባብረን በመስራት ለሀገር እድገትና ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን
Jun 22, 2026 18
ባህር ዳር/ደብረ ብርሃን፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦በጠቅላላ ምርጫው አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ በማግኘት አሸናፊ ከሆነው ብልጽግና ፓርቲ ጋር ተባብረን በመስራት ለሀገር እድገትና ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የባህር ዳር እና የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወዳደሩበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ድምጹን በነጻነት በመስጠት መንግስት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በምርጫ ብቻ መመስረት እንዳለበት ያለውን ጽኑ ፍላጎቱን አሳይቷል። በዚሁ መሰረት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ይፋ አድርጓል። በምርጫው ውጤት ላይ ኢዜአ በባህር ዳር እና በደብረ ብርሃን ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች፤ በጠቅላላ ምርጫው አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ በቀጣይ ለህዝብ ዘላቂ ሰላምና ልማት አበክሮ ይሰራል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ከምርጫው በፊት ለህዝብ ቃል በገባው መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮችን ለይቶ መስራት እንዳለበትም ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ከፓርቲው ጋር ተባብረው በመስራት በሀገር እድገትና ብልጽግና ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ነው ያረጋገጡት። የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ አቶ በትግሉ ተስፋሁን እንዳሉት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ያስቻለ እንቅስቃሴ በተግባር ተስተውሏል። በምርጫው አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ በማግኘት አሸናፊ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት ሲመሰርት ከምርጫ በፊት በገባው ቃል መሰረት ሰላምን ማጽናት እንዳለበት ገልጸዋል። እንዲሁም የህዝብን የላቀ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ሥራዎችን በማፋጠን የህዝብ አለኝታነቱን ዳግም ማረጋገጥ አለበት ብለዋል። በተመሳሳይ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎችም በምርጫው ካሸነፈው ብልጽግና ፓርቲ ጋር ተባብረው በመስራት በሀገር እድገትና ብልጽግና ላይ የራሳቸውን አሻራ እንደሚያሳርፉ አረጋግጠዋል። ከከተማው ነዋሪዎች መካከል የአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ነዋሪ አቶ ሀብታሙ ሞገስ እንዳሉት፣ በጠቅላላ ምርጫው አብላጫ ድምጽ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ማረጋገጥ ላይ አተኩሮ መስራት አለበት። ለምርጫው ያደረጉትን ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም ከፓርቲው ጋር በልማት በመተባበር ለሀገር እድገት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል። በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ጊዮርጊስ ቀበሌ ነዋሪ መቶ አለቃ ሰለሞን ዘለቀ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በህዝብ የተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ዳር ለማድረስ መትጋት አለበት። እርሳቸውም የሚመሰረተው መንግስት የሀገርን ሰላም በዘላቂነት በማረጋገጥ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። የጠባሴ ክፍለ ከተማ መሳለሚያ ቀበሌ ነዋሪ ወጣት እጅጋየሁ ሽፈራው በበኩሏ እንዳለችው፤ በህዝብ ድምጽ የተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቱን በሥራ ዕድልና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ የገባውን ቃል በተግባር ማሳየት አለበት። እንደ ወጣትነቷ ባላት እውቀትና ልምድ በፈጠራና በቴክኖሎጂ ላይ አተኩራ በመስራት በሀገር የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራዋን ለማሳረፍ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግራለች። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። የምርጫው ውጤት ይፋ መደረጉን ተከትሎም ብልጽግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፤ ፓርቲው በቅድመ ምርጫ ለህዝብ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት እንደሚያገለግልም አረጋግጧል ፡፡
የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን-ወጣቶች
Jun 22, 2026 30
አምቦ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ከአሸናፊው ፓርቲ ጎን በመቆም የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአምቦ ከተማ ወጣቶች ገለጹ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ከተማ ወጣቶች፤ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ከአሸናፊው ፓርቲ ጎን በመሆን የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወጣት ሽብሩ ነገሪ፤ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚችሉና ቀደም ሲል በሀገርና በክልል ደረጃ የተጀመሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብሏል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀዱ ግዙፍ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ ከፓርቲው ጎን በመሆን የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል። በከተማዋ በሁሉም ዘርፎች እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎችን ለማገዝ መዘጋጀቱን የገለጸው ደግሞ ወጣት ዮሐንስ ሚደቅሳ ነው። ከአሸናፊው ፓርቲ ጋር በመሆን በተጀመሩ የልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የአካባቢውን ወጣቶች በማስተባበር የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ወጣት ጭምዴሳ ነገሪ በበኩሉ፤ አብላጫ የምክርቤት መቀመጫ ያገኘው ፓርቲ ከዚህ ቀደም ዜጎች ሲያነሷቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅበታል ብሏል። የተጀመሩና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲቀጥሉ የበኩሉን እንደሚወጣም ገልጿል።
የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ፤ ሴኔጋል ከኖርዌይ፡አልጄሪያ ከጆርዳን
Jun 22, 2026 50
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ 9 እና 10 ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። በምድብ ዘጠኝ ኖርዌይ ከሴኔጋል በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ኖርዌይ ኢራቅን 3 ለ 1 ስትረታ ሴኔጋል በፈረንሳይ 3 ለ 1 ተሸንፋለች። ኖርዌይ ካሸነፈች ጥሎ ማለፍ መግባቷን ታረጋግጣለች። የምዕራብ አፍሪካዋ ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ህልሟን እውን ለማድረግ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባታል። በዚሁ ምድብ ፈረንሳይ ከኢራቅ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ በፊላደልፊያ ስታዲየም ይጫወታሉ። የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት ያገኘችው ፈረንሳይ ድል ከቀናት ወደ ጥሎ ማለፉ ትገባለች። ኢራቅ በውድድሩ ላይ ለመቆየት ከጠንካራዋ ፈረንሳይ ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባታል። በምድብ 10 ጆርዳን ከአልጄሪያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታቸው ጆርዳን በኦስትሪያ 3 ለ 1፣ አልጄሪያ በአርጀንቲና የ3 ለ 0 ሽንፈት አስተናግደዋል። ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይፋለማሉ። አሸናፊው ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ተስፋውን ያለመልማል። በዚሁ ምድብ አርጀንቲና ከኦስትሪያ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በዳላስ ስታዲየም ይጫወታሉ። የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያሸነፉት ሁለት ሀገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። ጨዋታውን የሚያሸንፈው ሀገር ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱን ያረጋግጣል።
በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስቀጠልና ማጠናቀቅ፣ ከብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው
Jun 22, 2026 39
ጅግጅጋ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስቀጠልና ማጠናቀቅ፣ ከብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው ሲሉ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የምርጫውን ውጤት ይፋ መሆን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች፤ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ አክለውም፤ ለሀገሪቱ ዕድገትና ልማት መጎልበት ሕዝቡም ከፓርቲው ጎን በመቆም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ አደን ዩሱፍ እንደተናገሩት፤ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡትን የለውጥ ውጤቶች ማስቀጠል የአሸናፊው ፓርቲ ሃላፊነት ነው። ለውጦቹን በመደገፍም ለሀገራቸው ልማት የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው ነዋሪ አቶ መሀመድ አብዲ በበኩላቸው፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያከናውናቸው የነበሩ የልማት ሥራዎችን የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥና በምግብ ራስን ለመቻል የሚያስችል በመሆኑ፣ በቀጣይም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል። ፓርቲው በውኃ ተደራሽነት፣ በከተሞች መሠረተ-ልማት ማስፋፋትና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ረገድም የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርጎ መሥራት እንዳለበት አክለው ገልጸዋል። በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎትና ለምርታማነት እንዲበቁ በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ የገለጸው ደግሞ ወጣት አህመድ ኢብራሂም ነው። የመንግሥት ሠራተኞችን ተጠቃሚነት ማሳደግና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት አቅማቸውን በማጎልበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚገባም ገልጿል። ነዋሪዎቹ የመንግሥትን የልማት ጥረቶች በመደገፍና የልማት ሥራዎች እንዲጠናከሩ በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ አሸናፊ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቧል። በመልእክቱም በአጠቃላይ ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር፣ ምርጫ የሥልጣን መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዟችንን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት አጠናክረን ለመቀጠል ለተከበረው ሕዝባችን ዳግም ቃላችንን እናድሳለን ሲል ማረጋገጡ ይታወሳል።
በነቀምቴ ከተማ ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተዘጋጅተዋል
Jun 22, 2026 50
ነቀምቴ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦በነቀምቴ ከተማ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን የከተማው ግብርና ፅህፈት ቤት ገለጸ። የነቀምቴ ከተማ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ከድር፤ በከተማዋ ዘንድሮ ለምግብነት፣ ለአፈር ለምነት፣ ለከተማ ውበትና ለደን ልማት የሚውሉ 790 ሺህ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በከተማው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጀመረ ወዲህ በተተከሉ ችግኞች ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ኃላፊው ገልጸዋል። በዚህም የተራቆቱ መሬቶችን በዕፅዋት ለመሸፈን፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም የኅብረተሰቡን ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ባህል ለማጠናከር ተችሏል ብለዋል። የታቀደውን ግብ ለማሳካትም በግል፣ በመንግሥት እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት በሚንቀሳቀሱ 13 የችግኝ ጣቢያዎች ውስጥ ችግኞቹ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የዘንድሮው የችግኝ ተከላ በ15 ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ በዚሁ መሬት ላይ ከ700 ሺህ በላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል። በከተማዋ 65 ሺህ ነዋሪዎች በችግኝ ተከላው ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ተከላው በይፋ መጀመሩን አንስተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ የአየር ንብረት ሚዛንን ከመጠበቅ ባለፈ፣ እስካሁን ከ150 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉንም ኃላፊው ጠቅሰዋል። የከተማዋ የጨለለቂ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አበበ ኢድሪስ፣ ለአመታት በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ከራሳቸው አልፈው ልጆቻቸው ዛፍ የመትከል ባህል እንዲያዳብሩና የተተከሉትን እንዲንከባከቡ የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። የበኬጀማ ቀበሌ ነዋሪ አቶ እውነቱ ኃይለየሱስ በበኩላቸው፣ በየዓመቱ በችግኝ ተከላው ላይ አሻራቸውን በማኖር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በተለይም ችግኝ መትከል ብቻ በቂ እንዳልሆነ የገለጹት አቶ እውነቱ፣ የመንከባከብ ሥራም በዚያው ልክ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ በመሆኑ በከተማዋ ተጨባጭ ለውጥ እየታየ ነው ብለዋል። በዚህም ዝናብ ጊዜውን ጠብቆ እንዲዘንብ፣ ወንዞችና የደረቁ ኩሬዎች እንዲሞሉ እንዲሁም አካባቢው ከቀድሞው ይበልጥ ለምና አረንጓዴ እንዲላበስ ማገዙን ጨምረው ገልጸዋል።
ፖለቲካ

አሸናፊ ሆኖ ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲና በምርጫው ለተሳተፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ -ኢዜማ
Jun 22, 2026 85
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ መሪ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም በውድድሩ ተሳትፋችሁ የሕዝብ ውክልናን ላሳካችሁ ተፎካካሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ(ኢዜአ) ገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው መግለጫው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ በአብዛኛው የምርጫ ክልሎች አሸናፊ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል። ይሄንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ(ኢዜማ) ዛሬ ባስተላለፈው መልዕክት ፓርቲው በተወዳደረባቸው ቦታዎች 13 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና 73 የክልል እና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በማግኘቱ ለአባሎቹ እና ለደጋፊዎቹ እንኳን ደስ ያላችሁ ብሏል። በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ባገኘው ውጤትም በሃገር አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ ማጠናቀቁን ገልጿል። ስኬቱን ያስመዘገቡ የፓርቲውን ዕጩዎች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ያመሰገነው ፓርቲው ከቀጣዩ ምርጫ በፊት ባሉት ዓመታት ጠንካራ ጎኖቹን በማስቀጠል ክፍተቶቹን በስትራቴጂ እና ሌሎች አስፈላጊ ተግባራት በመሙላት ተጨባጭ የተፎካካሪ ፓርቲነት ሚናውን ጊዜ ሳያባክን የሚጀምረው ዛሬ መሆኑንም ገልጿል። በነዚህ ዓመታት ቀደም ሲል ስናደርገው እንደነበረ ሁሉ ብሔራዊ ጥቅሞችን በሚያሣኩ ጉዳዮች ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃይል ጋር በመተባበር የምንንቀሳቀስበት ይሆናል ብሏል። መፎካከሪያ አጀንዳዎች ላይ ማኅበረሰባችንን በሚመጥን ጨዋነት ልዩነቶቻችንንና ትችቶቻችንን እያቀረብን የጀመርነውን ጤናማና ዘመናዊ የፖለቲካ ባሕል የማዋለድ ተግባራችንን በተጠናከረ መልኩ የምንቀጥልበት እንዲሁም ለተጨማሪ ስኬት የምንንደረደርበት እንደሚሆን ቃል እንገባለን ሲልም ገልጿል። ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ለተመረጠው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም በውድድሩ ተሳትፋችሁ የሕዝብ ውክልናን ላሳካችሁ ተፎካካሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ብሏል ፓርቲው በመልዕክቱ። አሸናፊው ፓርቲ ከዛሬ ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባትና ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንዲሠራ፤ ለሀገር እድገትና ለውጥ ጠቃሚ ሀሳቦች ከማንኛውም ወገን ሊገኙ እንደሚችሉ በመረዳት አማራጭ ሃሳቦችን እንዲሰማ ጠይቋል። እንዲሁም ትችቶችን በሆደ ሰፊነት እያስተናገደ ሀገራችን የሚያስፈልጋትን ዴሞክራሲ በጋራ እንድንገነባ ጥሪ እናቀርባለን ሲልም ኢዜማ ባስተላለፈው መልዕክት ገልጿል።
ብልጽግና ፓርቲ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበርና በዲፕሎማሲ ያመጣውን እመርታ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
Jun 22, 2026 61
አርባ ምንጭ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ብልጽግና ፓርቲ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር፣ በዲፕሎማሲ፣ በልማትና በዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ያመጣውን እመርታ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ ውጤቱን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች፤ ብልጽግና ፓርቲ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሀገር የመምራት እድል ማግኘቱ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል መምህር መስፍን ብርሃኑ እና ወይዘሮ ስሜነሽ መለሰ፤ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ባለፉት ዓመታት የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር፣ በዲፕሎማሲ፣ በልማትና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ስኬታማ መሆኑን አንስተዋል። በሀገሪቱ የተገነቡና አሁንም በግንባታ ላይ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችም የፓርቲው የስኬት መገለጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ፓርቲው በቀጣይ አምስት ዓመታት በተለይም ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር፣ በዲፕሎማሲ፣ በልማትና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያመጣውን እመርታ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። የከተማዋ ነዋሪ አቶ ተስፋለም ባቤና፤ ብልጽግና ፓርቲ ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም ከመስራት ባሻገር በገበታ ለሀገርና ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በዲጂታል ልማትና ሌሎችም ተጨባጭ እድገት ማምጣቱን ተናግረዋል። በመሆኑም እነዚህን መልካም ጅምሮች አጠናክሮ በመቀጠል ለሀገር እድገትና ለዜጎች ተጠቃሚነት ይበልጥ መስራት እንዳለበት አንስተዋል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ አሸናፊ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቧል። በመልዕክቱም በአጠቃላይ ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር፣ ምርጫ የሥልጣን መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዟችንን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት አጠናክረን ለመቀጠል ለተከበረው ሕዝባችን ዳግም ቃላችንን እናድሳለን ሲል አረጋግጧል።
ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በሁሉም የልማት ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተዘጋጅተናል
Jun 22, 2026 71
ሀዋሳ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ አብላጫ ድምጽ በማግኘት መንግስት ከሚመሰርተው ብልጽግና ፓርቲ ጋር በሁሉም የልማት ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተዘጋጅተናል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ በማግኘት ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ሀገሪቱን የሚመራበትን ዕድል ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። ኢዜአ በሀዋሳ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለፁት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰጠነው ድምጽ አሸናፊ ከሆነው ብልጽግና ፓርቲ ጋር በሁሉም የልማት መስኮች በጋራ እንሰራለን። የሀዋሳ ከተማ ነዋሪው አቶ መስፍን ታሪኩ፤ በጠቅላላ ምርጫው ይመራናል፤ ያስተዳድረናል፤ ላልነው ፓርቲ ድምጻችንን ሰጥተናል ብለዋል። በሰጠነው ድምጽ መሰረት አብላጫ ድምጽ በማግኘት መንግስት ከሚመሰርተው ብልጽግና ፓርቲ ጋር በሁሉም የልማት ዘርፎች በትብብር ለመስራት ተዘጋጅተናል ብለዋል። ፓርቲው ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ መልኩ የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትገኝ የጀመረውን ተግባር በትኩረት እንዲያስቀጥልና የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲጠናከሩ ጠይቀዋል። አቶ ሚካኤል ቢቸና በበኩላቸው፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሌት ብርድ የቀን ሀሩር ሳይበግራቸው ይመራናል ይበጀናል ያሉትን ፓርቲ መምረጣቸውን አስታውሰዋል። የመረጥኩት ፓርቲ በማሸነፉ ደስተኛ ነኝ ያሉት አቶ ሚካኤል በቀጣይ መንግስት በመመስረት የሚያከናውናቸው የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ ከፓርቲው ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እንዲፋጠኑ የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም እንዲሁ። ግንቦት 24/2018 ዓ.ም በተካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ መስጠታቸውንና ድምጽ የሰጡት ፓርቲ አሸናፊ በመሆኑ ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው የተናገሩት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪው አቶ ምርጋ ሃርሶ ናቸው። ፓርቲው መንግስት መስርቶ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሊሰራ ያቀዳቸው ተግባራት እንዲሳኩ እንደ ዜጋ የሚጠበቅብኝን ሁሉ እወጣለሁ ብለዋል።
ከፓርቲው ጋር በመሆን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንሰራለን- የሐረር ከተማ ነዋሪዎች
Jun 22, 2026 60
ሐረር ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በመሆን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንሰራለን ሲሉ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት አስታውቋል። በዚህም መሰረት ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በመሆን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክረው ለማስቀጠል ይሰራሉ ። ከአስተያየት ከሰጡት ነዋሪዎቹ መካከል አቶ ጀማል መሐመድ እንዳሉት፤ ብልጽግና ፓርቲ በኮሪደር ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች የልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጦችን እያስመዘገበ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ጠቁመው፤ ህዝቡም ከፓርቲው ጋር በመሆን የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል። አካል ጉዳተኛው አቶ ኢምራን አህመድ በበኩላቸው፤ ፓርቲው በማሸነፉ መደሰታቸውን ተናግረው፤ ቀጣይ አምስት ዓመታት ፓርቲው የተሻለ ስራ የሚያከናውንበት መሆኑን ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የሕዝብን ተጠቃሚነት ይበልጥ በሚያጎለብት መልኩ በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተሳትፈን ድምጻችን ዋጋ እንዳለው በግልጽ አይተናል፤ ብልጽግና ፓርቲ በማሸነፉም ተደስተናል ያለችው ደግሞ ወጣት የአብስራ ደሳለኝ ናት። ፓርቲውም በቀጣይ አምስት ዓመታት የተሻለ ስራ እንደሚያከናውን ያላትን ተስፋ በመግለጽ “እኔም እንደ ወጣት የሚጠበቅብኝን አስተዋጽኦ አበረክታለሁ” ብላለች፡፡ ወጣት አብዱለዚዝ ሸኪብ በበኩሉ "ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱን ወደፊት እያሻገረ የሚገኝ ፓርቲ ነው፤ በዚህም በቀጣይ አምስት ዓመት የተሻለ የልማት ተግባራትን በማከናወን የህዝብ ተጠቃሚነትን ያጎለብታል የሚል እምነት አለኝ" ብሏል። ፓርቲው በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና በመፈጸም “ቃልን በተግባር አሳይቷል” ያለው ወጣት አብዱለዚዝ፤ በቀጣይም ከፓርቲው ጋር የተጀመረውን የልማት ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ አሸናፊ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቧል።
ፓርቲው በጠቅላላ ምርጫው ማሸነፉ የተጀመሩ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶችን ዳር ለማድረስ ዕድል የሚፈጥር ነው
Jun 22, 2026 152
ጭሮ/ነጌሌ ቦረና/ጊምቢ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ የብልፅግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉ የጀመራቸውን ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ገለፁ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የብልፅግና ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል። በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በኮሪደር ልማት፣ በግብርናው ዘርፍ እንዲሁም በቱሪዝምና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ረገድ ሀገራዊ ለውጥ የሚያመጡ ሰፋፊ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ፓርቲው እነዚህን ፕሮጀክቶች በተቀናጀ እና በተሟላ ሁኔታ ለማስቀጠል እንዲሁም ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የህዝብ ይሁንታ አግኝቷል። ነዋሪዎቹ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ በተለይ በዚህ ዓመት የተጀመሩ ትላልቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያረጋግጡ በመሆናቸው፣ አሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ ፕሮጀክቶቹን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት ሊሰራ ይገባል። የጭሮ ከተማ ነዋሪ አቶ ቡሹራ ጁሃር እንዳሉት፤ ብልፅግና ፓርቲ የጀመራቸውን እንደ ማዳበሪያ ፋብሪካ፣ ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ እና የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ልማት ያሉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት አለበት። "በምርጫ ማሸነፍ ታላቅ ህዝባዊ አደራ መሸከም ነው፤" ያሉት አቶ ቡሹራ፣ በዚህ ረገድ የህዝቡን የልማት ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል። አክለውም በምርጫው አብላጫ ድምፅ በማጣት የተሸነፉ ፓርቲዎችም የሀገሪቱን ዕድገትና ለውጥ ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የከተማው ነዋሪ አቶ አሚን አሊዪ በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው ማሸነፉ የሀገር አንድነትን ለማጠናከር፣ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈንና የበለፀገች ሀገር ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት እንዲያሳካ ዕድል እንዳስገኘለት ተናግረዋል። ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ውጤቱን በጋራና በፀጋ በመቀበል፣ ከተመራጩ ፓርቲ ጋር ሀገሪቱን ለማሸጋገር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል። ያህያ አደም በበኩሉ፤ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘውን ዳግም ዕድል በመጠቀም በግብርና፣ በከተሞች ልማት እና በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ያስመዘገበውን ውጤት በማጠናከር ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ተግቶ ሊሰራ እንደሚገባ ገልጿል። ነዋሪዎቹ በሁሉም መስኮች ሀገሪቱን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ብልፅግና ፓርቲ ለሚያደርገው ጥረት ድጋፋቸውን እንደሚሰጡም አረጋግጠዋል። የነጌሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት በጸጋ በመቀበል ለሀገር ልማትና እድገት በትብብር እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በከተማው የሀሎ ጋፍትሮ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ገመቹ ገቢስ፤ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ ምርጫ መካሄዱን ጠቅሰው፣ አሸናፊው ፓርቲ ብዙ ስራ እንደሚጠበቅበት አውቆ መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል። የዚሁ ከተማ የመልካ ኦዳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ወንዶሰን ፈለቀ በበኩላቸው፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ የነበረው ህዝባዊ ሰልፍ በታሪክ የማይረሳ ክስተት እንደነበርም አስታውሰዋል። በምርጫው ያልተሳካላቸው ፓርቲዎችም ውጤቱን በጸጋ በመቀበል ህዝባቸውንና ሀገራቸውን ሊያስቀድሙ እንደሚገባና አሸናፊው ፓርቲም የተቀበለውን የህዝብ አደራ ለመወጣት መትጋት አለበት ብለዋል። የምዕራብ ወለጋ ዞን ነዋሪዎችም ብልጽግና ፓርቲ ህዝብን ማዕከል ባደረጉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባው ገልጸዋል። የእናንጎ ከተማ ነዋሪ አቶ አድማሱ ታመነ እንዳሉት፤ አሸናፊው ፓርቲ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ይመልሳል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። የላሎ አሳቢ ወረዳ ነዋሪ አቶ ባህሩ ኢማና በበኩላቸው፤ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ቃል የተገቡልን ልማቶች በተግባር እንዲፈጸሙ ከተመራጩ ፓርቲ እንጠብቃለን ሲሉ ገልጸው፤ ፓርቲው ለማከናወን ላቀዳቸው የልማት ስራዎች ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።
የህዝብ ድምጽ አሸንፏል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታለች - የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
Jun 22, 2026 146
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ) ፦ የህዝብ ድምጽ አሸንፏል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታለች ሲል የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት አብዛኛውን ድምጽ ብልጽግና ፓርቲ ማሸነፉን ትላንት አስታውቋል። ይሄንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በምርጫው ለተሳተፉ ሁሉ የምስጋና መልዕክት አስተላልፏል። ሙሉ መልዕክቱ እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ከአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የተላለፈ የምስጋና መልዕክት የህዝብ ድምጽ አሸንፏል፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታለች! መላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲን በማፅናታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን! የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለፓርቲያችን ብልፅግና የሰጣችሁት ድምፅ የቃል ኪዳናችን ማሰሪያ በማድረግ የጣላችሁብን አደራ በላቀ ስኬት ለመመለስ እንተጋለን። ይህ ምርጫ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት የሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሻገረበት ደማቅ የታሪካችን አካል ሆኖ ተመዝግቧል ። በመዲናችን አዲስ አበባ በተደረገው የከተማ ምክር ቤት ምርጫ፣ ፓርቲያችን ብልፅግና ከጠቅላላው 158 መቀመጫዎች ውስጥ 134፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ23ቱ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ 20 መቀመጫዎችን በማግኘት የህዝብን ሙሉ አመኔታና አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸንፏል። በሌላ በኩል ከ158 የከተማ ምክርቤት መቀመጫዎች ውስጥ 11 የተፎካካሪ ፓለቲካ ፒርቲዎች 23 የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮች ያገኙ ሲሆን አዲስ አበባ ከምትወከልበት ከ23ቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች 2 እንዲሁም የግል ተወዳዳሪ 1 ወንበሮችን ማሸነፍ ችለዋል። ይህ እጅግ አስደናቂ ዉጤት እያደገ የመጣዉን የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እና የህዝብን ፍትሐዊ ዳኝነት ያሳያል። በጥቅሉ ፓርቲያችን በአብላጫ ድምፅ ቢያሸንፍም በዋናነት ያሸነፈዉ መላው የመዲናችን ነዋሪ ፣ ሰላም እንዲሁም ልማት እና እያደገ የመጣዉ የዴሞክራሲ ባህል ነው። የተከበራችሁ መራጮቻችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊት እስከ ለሊት በምርጫ ጣቢያዎች በመሰለፍ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ እንዲጠናቀቅና ለብልፅግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በመስጠት እምነት ለጣላችሁብን ለቀጣዩ ጉዟችንም የህዝብ አደራን በአግባቡ እንድንወጣ አቅማችን ለሆናችሁ በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በቀጣዩ የ5 ዓመቱ ጉዟችን ህዝባችን የሰጠንን ታላቅ አደራ በገባነው ቃል መሠረት ሌት ተቀን በመሥራት፣ የከተማችንን ብሎም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ተግባራዊ ምላሽ እንሰጣለን። በተለመደው መልኩ ከህዝባችን ጋር በመተባበር በከተማችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞን በማሳለጥ የህዝባችን ኑሮ እና አኗኗር ለመለወጥ ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን! ይህ ድል የብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል ነው! ዲሞክራሲን እያፀናን ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ እያስተናገድን፣ በአንድነትና በፓርቲያችን መሪነት ወደ ላቀ ከፍታ እንጓዛለን። ምርጫውን በማስፈጸም፣ በመታዘብ ፣ ሰላምን በማስጠበቅ ዉጤታማ ስራ የሰራችሁ እንዲሁም የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም በማሳየት ረገድ የሀገሪቱን ህግና ስርዓት ተከትላችሁ የዘገባችሁ የሚዲያ ተቋማት ከሁሉ በላይ የሀገራችሁ ዴሞክራሲ አንድ እርምጃ ወደፊት እንዲራመድ የበኩላችሁን የተወጣችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! በመጨረሻ በሀገር አቀፍም ሆነ በከተማ ደረጃ የፖለቲካ ልዩነት ወደ ፖሊሲ አማራጭ በማሳደግ በዚህ ምርጫ ላይ ተፎካክራችሁ በህዝብ ይሁንታ ወንበር በማግኘት የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል ለመሆን የበቃችሁ የ11 ፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎችና አንድ የግል ተወዳዳሪ በሰላማዊ መንገድ ህዝባችሁን ለማገልገል ዕድል በማግኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን ። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! እንኳን ደስ አላችሁ! የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በህዝብ በይሁንታ የተሰጠውን ድምፅ እናከብራለን - የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
Jun 22, 2026 111
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ) ፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በህዝብ በይሁንታ የተሰጠውን ድምፅ እናከብራለን ሲል የወሎ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወዴፓ) ገለጸ። ፓርቲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም በጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ቀደም ሲል መግለጹን አስታውሶ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተገለጸው ውጤት መሰረትም በህዝብ ይሁንታ የተሰጠውን ድምጽ እንደሚያከብር አስታውቋል። በቦርዱ መግለጫ መሰረት የብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለከተማና ክልል ምክር ቤቶች መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ማግኘቱን በማንሳት ለፓርቲው አመራሮች ፣ለአባላትና ለመራጩ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል። በቀጣይ አምስት ዓመታትም ኢትዮጵያ ያሉባት ችግሮች ሙሉ በሙሉ የሚቀረፉበት የጀመረችው ምክክር በውጤት የሚጠናቀቅበት እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል። የሰለጠነ የዲሞክራሲ ስርአት ጅማሮ ላይ ላለችው ሀገራችን የሰላምና የእድገት የመሻገር ጊዜ እንዲሆን እየተመኘን ፓርቲያችን የሀገር ሉአላዊነትን ፣ የልማትና የእድገት ጉዞን የሚያደናቅፉ የውጭም ሆነ የውስጥ የጥፋት ሀይሎችን ከመንግስት ጎን ቆመን የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን ሲል ፓርቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

ማህበራዊ
ህዝቡ የጣለብንን ታላቅ ኃላፊነት ከግብ ለማድረስና የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Jun 22, 2026 124
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ህዝቡ የጣለብንን ታላቅ ኃላፊነት ከግብ ለማድረስ፣ አብሮነትን ለመገንባትና የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ በትጋት እንሰራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። የአራዳ የበጎነት መንደር የአቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሂዷል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ፣ የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለሃብቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ የአራዳ በጎነት መንደር ግንባታ ህብረተሰቡ የጣለብንን እምነትና የሰጠንን ድምፅ የቃልኪዳን ውል አድርገን በተቀበልን ማግስት መጀመሩ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል። ግንባታው "ገዳም ሰፈር" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚከናወን የመልሶ ማልማት ስራ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ ባለዘጠኝ ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ ህንፃ እና ባለአራት ወለል የገበያ ማዕከል ግንባታ እንደሚከናወን አስታውቀዋል። የገዳም ሰፈር አካባቢ ቀደም ሲል ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ፣ ያልዘመኑና ከተማዋን የማይመጥኑ ቤቶች የነበሩበት ቢሆንም፤ ታሪካዊ ቅርሶች ያሉበትና በርካታ ቱሪስቶችን የሚያስተናግድ ስፍራ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ይህ የአራዳ በጎነት መንደር ለህብረተሰቡ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ፣ የነዋሪዎችን ኑሮና አኗኗር በእጅጉ የሚያሻሽል መሆኑን ገልፀዋል። ባለፉት ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ሆነን ውጥኖቻችንን በማሳካት ውጤት አስመዝግበናል ያሉት ከንቲባዋ ውብ፣ ፅዱ፣ አረንጓዴና ለነዋሪዎች ምቹ ከተማን ለመፍጠር የጀመርነው የ24/7 ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በከተማዋ የበጎነት እሴት ከቀን ወደ ቀን እየጎለበተ መምጣቱን የገለጹት ከንቲባዋ፣ ይህ የበጎነት መንደርም ከተማ አስተዳደሩ ከባለሃብቶች ጋር በመተባበር የሚገነባው መሆኑን አስገንዝበዋል። በተጨማሪም በ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 2 ሺህ 500 የመኖሪያ ቤቶችን ከመገንባት ባለፈ ሌሎች በርካታ የበጎ ተግባር ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ የሕብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማዋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በርካታ አካላት በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ46 ሺህ በላይ ቤቶች ተገንብተው ከ200 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል። ለዚህም ስራ ስኬት ከ55 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት በገንዘብ፣ በእውቀትና በጉልበት ማዋል መቻሉን አብራርተዋል። በ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ መርሃግብሮች ተቀርፀው ወደ ትግበራ እንደሚገቡም አስታውቀዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል
Jun 22, 2026 79
ባህር ዳር ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ገለጸ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተወካዮች እና በክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ፓርቲው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቦ ሁለንተናዊ ብልፅግናን በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዞውን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ በአንድነትና በቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ቃል ገብቷል። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ፍሬሰላም ዘገዬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሀገር የመምራት እድል በማግኘቱ ደስታ ተሰምቷቸዋል። "በክልሉ ከአራት ሚሊዮን በላይ አካል ጉዳተኞች ይገኛሉ" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ የአካል ጉዳተኞች ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከማድረግ ባሻገር በመምረጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በዚህም አሸናፊው ብልጽግና ፓርቲ የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል ብለዋል። በተለይም ፓርቲው አካል ጉዳተኞችን ወደ ውሳኔ ሰጪነት እንዲመጡ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በኩል ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አረጋግጠዋል። በየደረጃው ባለ የመንግስት እርከን የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎት ያማከለ ውክልናን ለማስፈን ከአሸናፊው ብልጽግና ፓርቲ ጋር በመተባበር ፌዴሬሽኑ ይሰራል ብለዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ምቹ፣ ተደራሽና አካታች በማድረግ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን የአሸናፊ ፓርቲው ዋነኛ የቤት ሥራ መሆኑን አስረድተዋል። የአካል ጉዳተኞችም ድጋፍ እንዲደረግላቸው መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣ በሀገራቸው ሰላምና ልማት ላይ የላቀ አበርክቶ እንዲኖራቸው ተቀናጅተው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል። በአካል ጉዳተኞች ዘንድ ያለውን እውቀት፣ ጥበብና አቅም ለህብረ ብሔራዊ አንድነትና ጠንካራ ሃገረ መንግስት ግንባታ ለማዋል በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አክለዋል።
የኢትዮጵያ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ትስስር በማጠናከር የወጣቶችን የሀገር ግንባታ ሚና እያጎለበተ ነው
Jun 21, 2026 635
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር የወጣቶችን የሀገር ግንባታ ሚና እያጎለበተ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በርካታ የሰው ተኮር ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን፣ በተለይም የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የማካሄድ ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ መጥቷል። ከተለያዩ የበጎ ፈቃድ ዘርፎች መካከልም አንዱ የሆነው ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በትኩረት እየተሰራበት የሚገኝ ዘርፍ ነው። ይህ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ፣ ሀገራቸውን በቅርበት ለማወቅና ለመገንዘብ ትልቅ ዕድል እየፈጠረላቸው ነው። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አሕመድ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከሁሉም አቅጣጫ የተውጣጡ ወጣቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው በጎ ተግባራትን እያከናወኑ ነው። ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ወጣቶችን በማቀራረብ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት የሀገር ግንባታ ገንቢ ሚናቸውን እየተወጡ ነው ብለዋል። ይህም በወጣቶች መካከል የባህልና እሴት ልውውጥን በመፍጠር ወጣቶች የሀገራቸውን መልክና ልዩ ገጽታዎች የማወቅ ዕድል እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዚህም ወጣቶች በጋራ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ይበልጥ እያጠናከረ መሆኑን ተናግረዋል። በ2014 ዓ.ም የተጀመረው ይህ መርሃ ግብር፣ ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ 5" በሚል መሪ ሀሳብ ለማከናወን ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። በሀገር ደረጃ የተጀመረው ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሁን ላይ በክልሎችና በዞኖች መካከል ልምድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እንዳደረገችው ሁሉ በበጎ ፈቃድ ሥራም የበለጸገ ባህልን በመገንባት ለዓለም ተምሳሌት ለመሆን እየሠራች መሆኑን አንስተዋል። በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብርም ወጣቶች በተደመረ አቅም በንቃት በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዋናው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ርቀው የሚገኙ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ቀጥለዋል
Jun 20, 2026 1115
ሀዋሳ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ ከዋናው የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ርቀው የሚገኙ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የፀሐይ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ። በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ሆኮ ወረዳ የሆዲ ቦኩ ከተማ አነስተኛ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። በፕሮጀክቱ ምረቃ ወቅት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም የማህበረሰቡን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉት ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። የዚሁ አካል የሆነውና በ230 ሚሊዮን ብር የተገነባው የሆዲ ቦኩ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 525 ኪሎ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ከ2 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል። የሲዳማ ክልል ውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ከበደ ጋኖሌ በበኩላቸው፤ የፕሮጀክቱ ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ነው ብለዋል። የኃይል አቅርቦቱም የሕብረተሰቡን የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ለማሻሻል ያስችላልም ብለዋል። እንዲሁም ኢኮኖሚውን በማነቃቃት የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግና ለከተማዋ ዕድገት የላቀ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ክንፈ ነጋሽ በበኩላቸው፣ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት ለታዳሽ ኃይል ልማት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በተለይም ከመደበኛው የኤሌክትሪክ መስመር የራቁ አካባቢዎችን የፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመገንባት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። በዚህ ሂደት በመላ አገሪቱ 43 የታዳሽ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በመገንባት ከ10 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል። 525 ኪሎ ዋት የሚያመነጨው የዛሬው የሆዲ ቦኩ ፕሮጀክት የውስጥ ለውስጥ መስመር ዝርጋታና ሦስት ትራንስፎርመሮች እንዳሉትም አስረድተዋል። በፕሮጀክቱ ምረቃ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ታድመዋል።
ኢኮኖሚ
የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን-ወጣቶች
Jun 22, 2026 30
አምቦ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ከአሸናፊው ፓርቲ ጎን በመቆም የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የአምቦ ከተማ ወጣቶች ገለጹ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአምቦ ከተማ ወጣቶች፤ የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፋጠኑ ከአሸናፊው ፓርቲ ጎን በመሆን የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወጣት ሽብሩ ነገሪ፤ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ጥያቄ መፍታት የሚችሉና ቀደም ሲል በሀገርና በክልል ደረጃ የተጀመሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብሏል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የታቀዱ ግዙፍ የልማት ስራዎች እንዲሳኩ ከፓርቲው ጎን በመሆን የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል። በከተማዋ በሁሉም ዘርፎች እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎችን ለማገዝ መዘጋጀቱን የገለጸው ደግሞ ወጣት ዮሐንስ ሚደቅሳ ነው። ከአሸናፊው ፓርቲ ጋር በመሆን በተጀመሩ የልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ እንዲሁም የአካባቢውን ወጣቶች በማስተባበር የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ወጣት ጭምዴሳ ነገሪ በበኩሉ፤ አብላጫ የምክርቤት መቀመጫ ያገኘው ፓርቲ ከዚህ ቀደም ዜጎች ሲያነሷቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅበታል ብሏል። የተጀመሩና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲቀጥሉ የበኩሉን እንደሚወጣም ገልጿል።
በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስቀጠልና ማጠናቀቅ፣ ከብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው
Jun 22, 2026 39
ጅግጅጋ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስቀጠልና ማጠናቀቅ፣ ከብልጽግና ፓርቲ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው ሲሉ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሕዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤቶች ብልጽግና ፓርቲ አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የምርጫውን ውጤት ይፋ መሆን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች፤ ብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ አክለውም፤ ለሀገሪቱ ዕድገትና ልማት መጎልበት ሕዝቡም ከፓርቲው ጎን በመቆም የድርሻውን ማበርከት እንዳለበት ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ አደን ዩሱፍ እንደተናገሩት፤ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡትን የለውጥ ውጤቶች ማስቀጠል የአሸናፊው ፓርቲ ሃላፊነት ነው። ለውጦቹን በመደገፍም ለሀገራቸው ልማት የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሌላኛው ነዋሪ አቶ መሀመድ አብዲ በበኩላቸው፤ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያከናውናቸው የነበሩ የልማት ሥራዎችን የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት ገልጸዋል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥና በምግብ ራስን ለመቻል የሚያስችል በመሆኑ፣ በቀጣይም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል። ፓርቲው በውኃ ተደራሽነት፣ በከተሞች መሠረተ-ልማት ማስፋፋትና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ረገድም የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማዕከል አድርጎ መሥራት እንዳለበት አክለው ገልጸዋል። በሀገሪቱ የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎትና ለምርታማነት እንዲበቁ በትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ የገለጸው ደግሞ ወጣት አህመድ ኢብራሂም ነው። የመንግሥት ሠራተኞችን ተጠቃሚነት ማሳደግና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት አቅማቸውን በማጎልበት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚገባም ገልጿል። ነዋሪዎቹ የመንግሥትን የልማት ጥረቶች በመደገፍና የልማት ሥራዎች እንዲጠናከሩ በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ አሸናፊ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ምስጋና አቅርቧል። በመልእክቱም በአጠቃላይ ብልፅግና ፓርቲ የገባውን ቃል ሳይሸራረፍ በመተግበር፣ ምርጫ የሥልጣን መቆናጠጫ ሳይሆን ሕዝብን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገያ ታላቅ አደራ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ታሪካዊ ጉዟችንን ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ትጋት፣ አንድነትና ቁርጠኝነት አጠናክረን ለመቀጠል ለተከበረው ሕዝባችን ዳግም ቃላችንን እናድሳለን ሲል ማረጋገጡ ይታወሳል።
ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤቶች መቀመጫ በማግኘት አሸናፊ መሆኑ የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን ለስኬት ለማብቃት ዕድል ይፈጥራል
Jun 22, 2026 80
ወልቂጤ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤቶች መቀመጫ በማግኘት አሸናፊ መሆኑ የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት ሥራዎችን ለስኬት ለማብቃት ዕድል ይፈጥራል ሲሉ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በእዚህም ፓርቲው ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች አብላጫውን መቀመጫ በማግኘት ማሸነፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የኢዜአ ሪፖርተር በወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሯል። ነዋሪዎቹ ፤ በምርጫው ከጅምሩ እስከመጨረሻው የታየው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደት በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርአት ጥሩ መሰረት እየያዘ መምጣቱን ያመላከተ ነው ብለዋል። በምርጫው ቀን ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም ከማለዳ እስከ እኩለሌሊት ረጃጅም ሰልፎችን ታግሰው ድምጽ እንደሰጡ አስታውሰው፣ በዚህም ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ሀይሉ ተሰማ፣ ወይዘሪት ሳድያ ኑረዲን እና አቶ መንግስቱ ባንቀስራ፤ በምርጫው ብልጽግና ፓርቲ አብላጫ የምክር ቤት መቀመጫ በማግኘት አሸናፊ መሆኑ ባለፉት ዓመታት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለስኬት ለማብቃት መልካም እድል መሆኑን ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በብልጽግና ፓርቲ የተመራው መንግስት ያከናወናቸው የልማት ሥራዎች ለኢትዮጵያ እድገትና ማንሰራራት መሰረት ያኖሩ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለላቀ ስኬት መትጋት እንዳለበት ተናግረዋል። በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲሳኩ፣ የከተሞችና የገጠር ኮሪደር ልማት ቀጣይነት እንዲኖረው እንዲሁም ለግብርና ምርታማነት ማደግ ብዙ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ለሀገር ልማት ስኬትና እድገት የመንግስት ጥረት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል። የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና እድገት እውን ለማድረግ ከመንግስት ጋር በተደመረ አቅምና በተባበረ ክንድ መስራት ይኖርብናል ሲሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ ሰላምና ዕድገትን ከማረጋገጥ የሚመነጭ ምክንያታዊ አጀንዳ ነው
Jun 21, 2026 666
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሕጋዊና ታሪካዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ ሰላምና ዕድገትን ከማረጋገጥ የሚመነጭ ምክንያታዊ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ረጅሙ የስልጣኔ ታሪክና ሃያልነት ከተፈጥሯዊ የባሕር በር ባለቤትነት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን የታሪክ ድርሳናት ከትበው ያስቀመጡት የአደባባይ ሃቅ ነው። የሀገር ውስጥ ባንዳና የውጭ ባዕዳን ታሪካዊ ጠላቶች የሸረቡት ሴራም የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ የባሕር በር ባለቤትነት በማሳጣት በሀገር ላይ ኢ-ፍትሐዊ በደል ተፈጽሟል። በኢትዮጵያዊያን ልብ ለሶስት አስርት ዓመታት ተዳፍኖ እንዳይነሳ ተደርጎ የቆየው የባሕር በር ባለቤትነትም በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ወሳኝ አጀንዳ ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትም ከፍተኛ የህዝብ ቁጥርን ከፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አጣምሮ ለያዘ ሀገር ምላሽን የሚሻ ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ ፍትሐዊ፣ መልክዓምድራዊና ምክንያታዊ ጥያቄ ነው። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ምሁራን፤ ኢትዮጵያ ከተፈጥሯዊና ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነቷ እንድትገለል የተደረገበት አጋጣሚ የሚያስቆጭ መሆኑን ገልጸዋል። በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-አመራርና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ጌትዬ ትርፌ(ዶ/ር)፤ የታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች የሴራ ጥምረት የባሕር በር ባለቤትነታችንን እንድናጣ አድርጓል ብለዋል። የግል ጥቅምን ከማስቀደም የተሻገር ርዕይ ያልነበረው የስልጣን ጥመኛ ቡድን የፈጸመው ክህደት የትውልድን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ በመስጠት በሀገር ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል መፈጸሙን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ከባሕር በር ባለቤትነቷ በግፍ መነጠሏም፤ በገቢና ወጪ ዓለም አቀፍ የንግድ ተወዳዳሪነትን ከማቀጨጭ ባሻገር ቀጣናውን የሽብርተኞች መፈንጫ ማድረጉን ገልጸዋል። ከሀገራዊ ለውጡ በፊትም ለሶስት አስርት ዓመታት ታሪካዊ፣ ሕጋዊና መልክ ዓምድራዊ ይዞታዋ በአጀንዳነት እንዳይነሳ የተደረገበት ትርክትም ዜጎችን አሳዝኖ የቆየ እንደነበር አስረድተዋል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ኢትዮጵያዊያን የጋራ አቋም በመያዝ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄን በስትራቴጂክ ብሔራዊ ጥቅም አጀንዳነት ማቅረባቸው የታሪክ ስብራትን የማረም ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን እያገኘ የመጣ የስትራቴጂክ ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነትም ቀጣናዊ ትብብርና ጥንካሬን በማጎልበት የሰላም፣ የኢኮኖሚ ዕድገትና የገበያ ትስስር መሰረት መሆኑን አብራረተዋል። በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ተመራማሪ ተመስገን ዋለልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባህር በር ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከስትራቴጂክ የባሕር በር ባለቤትነት መገለሏ ሶስት አስርት ዓመታትን በተሻገረ ዘመን በዜጎች ህይወት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የሎጂስቲክስ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን አስገንዝበዋል። በአሁኑ ወቅትም የሃያላኑ ዐይን ማረፊያ በሆነው የቀይ ባሕር ቀጣና ኢትዮጵያዊያን ታሪካዊና ሕጋዊ የባሕር በር ባለቤትነታቸውን ለማስመለስ የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ኢንስቲትዩቱ የፍትህ ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Jun 20, 2026 883
አዳማ፣ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኦሮሚያ ሕግ ምርምርና ፍትሕ ኢንስቲትዩት የፍትህ ዘርፉን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ። ኢንስቲትዩቱ የፍትህ ሪፎርሙን ለማሳካት ያካሄዳቸውን የምርምር ውጤቶች በግብዓት ለማዳበር የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ አባገዳ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ገዛሊ አባ ሲመል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በጥናትና ምርምር የተደገፉ የመፍትሔ ሐሳቦችን እያቀረበ ይገኛል። በመድረኩ ላይ በቁልፍ የፍትህ ዘርፍ ጉዳዮች ዙሪያ የተከናወኑ አምስት የተለያዩ የምርምር ውጤቶች እንደሚቀርቡ ተናግረዋል። ምርምሮቹም የፍትህ አካላት ስነ-ምግባር፣ የፌዴራልና የክልል የህግ ተፈፃሚነት ወሰን ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶች፣ በፍትህ ዘርፉ የዲጂታል አገልግሎት ዘመን የቋሚና ተዘዋዋሪ ችሎት አስፈላጊነት፣ እንዲሁም የህግ ትርጓሜና የተፈፃሚነት ወሰን የተመለከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህ የምርምር ውጤቶች ጠንካራ የፍትህ ስርዓት በመገንባት በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የፍትህ ዘርፍ ሪፎርም ለማሳካት ወሳኝ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተለይም በህግና በአሰራር ዙሪያ ያሉትን ክፍተቶች ለመድፈን በእጅጉ ያግዛሉ ብለዋል። የኦሮሚያ ህግ ምርምርና ፍትህ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አዱኛ ሙሐመድ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የፍትህ ስርዓትን ለማሻሻል እስካሁን ከ100 በላይ የምርምር ስራዎችን በማካሄድ በግብዓትነት እንዲያገለግሉ ማድረጉን ጠቁመዋል። በተለይም በዘርፉ የተጀመሩ የሪፎርምና የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ለማሳለጥ በጥናትና ምርምር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ የፍትህ ስርዓቱን አሰራር ለማዘመንና በቴክኖሎጂ ለመምራት የሚያስችሉ የምርምር ውጤቶች ለዛሬው መድረክ መቅረባቸውን ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ ከጥናትና ምርምር ስራዎች ጎን ለጎን፣ ብቁ የፍትህ አካላትን ለማፍራትና ጥራትን ለማረጋገጥ ለህግ ባለሙያዎች የስልጠናና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሯ አክለዋል። በመድረኩ ላይ በፌዴራልና በክልል የሕግ ወሰን ተፈጻሚነት ዙሪያ የተካሄደውን ምርምር ያቀረቡት አብዲሳ ጉርሜ (ዶ/ር)፤ የጥናቱ ውጤት በፌዴራልና በክልል የሕግ ተፈጻሚነት ረገድ የሚታዩ ውስንነቶችን በግልጽ በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመላከቱን አስገንዝበዋል። በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እና ከፌዴራል ፍትህ ኢንስቲትዩት የተጋበዙ ተመራማሪዎችና የህግ ምሁራን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር የመንግሥትና ሕዝብን አመኔታ የሚያጎለብት አቅም እየገነባ ነው
Jun 20, 2026 483
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር የመንግሥትና ሕዝብን አመኔታ የሚያጎለብት አቅም እየገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ''ዲጂታል ለልህቀት'' በሚል መሪ ሐሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ የሪፎርም ውጤቶችን የሚያሳየውን ኤግዚቢሽንና ጉባኤ መርቀዋል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን፤ በጋዝና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የፌደራል ተንቀሳቃሽ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በተጨማሪም አሥራ ሁለት ተቋማትን ከ27 አገልግሎቶቻቸው ጋር በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያን በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በፓናል ውይይት ላይ እንደገለጹት፤ የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን የአፍሪካና ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና አስተዳደር አብዮት ተሞክሮዎችን መቀመር ተችሏል። ይህም የኢትዮጵያን የመንግሥት አገልግሎቶች ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ዘመናዊ የፖሊሲና ፕሮግራም፣ አዋጅና ደንብ፣ መመሪያና ስታንዳርድ መቅረፅ የሚያስችል ሪፎርም ማካሄድ እንዳስቻለ ገልጸዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የፈጠረው ምኅዳር ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከብቁ የሰው ኃይል በማሰናሰል ፍሬያማ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፤ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ቴክኖሎጂን ከብቁ የሰው ኃይል ያቀናጀ ቁርጠኛ አገልግሎት ይፈልጋል ብለዋል። የኢትዮጵያ የመንግሥት አገልግሎትም ከቴክኖሎጂ ጋር የተጣጣመ ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር በመፍጠር የመንግሥትና ሕዝብን አመኔታ እያጎለበተ መሆኑን ገልጸዋል። የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድግ ምኅዳር ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የመሶብ አንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎትም የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ እያስገኘ ነው ብለዋል። የፌደራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ዓለማየው፤ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በመቅረፍ የአገልግሎት እርካታን እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። በአንድ ዓመት ውስጥ ተግባራዊ በተደረገው ውጤታማ የሪፎርም እርምጃም ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ 70 የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ወደ ሥራ ማስገባት እንደተቻለ ገልጸዋል። መሶብ ወደ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ተሸጋግሯል ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በቀጣይም ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎቶች በመሶብ የአንድ ማዕከል ለማካተት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል። በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የተቋማት ሪፎርም ዋና ዳይሬክተር አሰፋ በየነ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ሪፎርም አገልግሎትን በማዘመን የአገልግሎት ጥራትን የሚያሳደግ ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። የሪፎርሙን ዘላቂነትና ውጤታማነት ለማሳደግ የአመራር ቁርጠኝነትና የቴክኖሎጂ ትግበራ ቀጣይነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል። በቀጣይም የተቋማት አቅም ግንባታን በማጠናከር፣ የሰው ኃይልና ትውልድን ከቴክኖሎጂ ጋር የማብቃት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መክረዋል።
ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ርዕይ በሁሉም መስክ እየሰመረ ነው
Jun 20, 2026 923
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ርዕይ በሁሉም መስክ እየሰመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ''ዲጂታል ለልህቀት'' በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ የሪፎርም ውጤቶችን የሚያሳየውን ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል። ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን በጋዝና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የፌደራል ተንቀሳቃሽ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በተጨማሪም አሥራ ሁለት ተቋማትን ከ27 አገልግሎቶቻቸው ጋር በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያን በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክትም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የተቋማትን አገልግሎቶች ለማዘመን ከፍተኛ ሥራዎችን መሥራቱን ጠቅሰዋል፡፡ የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን የተወሰዱ ስኬታማ የሪፎርም ሥራዎችም ለኢትዮጵያ የኩራት ምንጭ በመሆን በቴክኖሎጂ የሚመራና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት እንደሚያስገኙ ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል። የሲቪል ሰርቪስ ቁልፍ የመንግሥት ተቋም ተቀይሮና ዘምኖ ማየትም ደስታን ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ወሳኝ የኢኮኖሚ መሠረተ ልማት ነው ብለዋል። ይህ ስኬት ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ምኞት ብቻ ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነው ሲሉ አብራርተዋል። ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያን ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና የባንክ ኢንዱስትሪ አገልግሎትና ምርታማነት በማዘመን ከፍተኛ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ስኬትም በማጠናከር፣ ልምድና ተሞክሮ ለአፍሪካውያን ወንድሞችና እህቶች በማካፈል እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት ወደፊት መጓዝ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶች ማሻሻያ ከመሶብ አንድ ማዕከል ወደ ተንቀሳቃሽ በመቀጠልም ወደ ሞባይል መተግበሪያ ያደረገው ፈጣን ሽግግር በአስደናቂ ፍጥነት የታጀበ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ ደረጃ ልክ እንደ መሶብ ሁሉም አገልግሎት በተቀናጀ ሥርዓት የሚሰጥበት የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አንድ ብላ የጀመረችው የመሶብ አገልግሎት አሁን ላይ 70 ደርሷል ብለዋል። ኢትዮጵያ ልምድ የወሰደችባቸው ሀገራት በአሥር ዓመታት ውስጥ ሰባ እንዳልደረሱ በመጠቆም፤ የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትም በአስደናቂ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን ተናግረዋል። የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያው በአፍሪካ በሁሉም መስክ የመጀመሪያው የተቀናጀ የአገልግሎት መተግበሪያ ነው ብለዋል። በመሶብ የአንድ ማዕከል መገልገል አስደናቂ ሆኖ ሳለ፤ ዜጎች በእጅ ስልካቸው ጉዳያቸውን ባሉበት ቦታና በየትኛውም ጊዜ መገልገል የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የመሶብ አገልግሎትም የመንግሥት አገልግሎትን ከአንድ ማዕከል ወደ ተንቀሳቃሽ፣ ከተንቀሳቃሽ ወደ የእጅ ስልክ ያሸጋገረና ጥቂት ሀገራት ብቻ የደረሱበት ስኬታማ ሥራ መሆኑን አንስተዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ በብዙ ጉዳዮች ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተምሳሌት የሚያደርጋት መሆኑን ጠቅሰው ብልፅግናን ለማረጋገጥ የበለጠ ትጋት የበለጠ ሥራ እና ልፋት እንደሚጠይቅም ጠቅሰዋል፡፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የኩራት ምንጭ እንዲሆኑ፣ ለልጆቿ ድህነትን የማታወርስ አገር መገንባት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ርዕይ በሁሉም መስክ እየሰመረ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውን የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያን መረቁ
Jun 20, 2026 629
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) '‘ዲጂታል ለልህቀት'’ በሚል ስያሜ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ፣ በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ዛሬ በይፋ መርቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል ሲሉም ገልጸዋል። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነውም ብለዋል። ይህን ስኬት እንድናጠናክር፣ ተሞክሯችንን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንድንጓዝ በማለት ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
ስፖርት
የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ፤ ሴኔጋል ከኖርዌይ፡አልጄሪያ ከጆርዳን
Jun 22, 2026 50
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ 9 እና 10 ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። በምድብ ዘጠኝ ኖርዌይ ከሴኔጋል በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ኖርዌይ ኢራቅን 3 ለ 1 ስትረታ ሴኔጋል በፈረንሳይ 3 ለ 1 ተሸንፋለች። ኖርዌይ ካሸነፈች ጥሎ ማለፍ መግባቷን ታረጋግጣለች። የምዕራብ አፍሪካዋ ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ህልሟን እውን ለማድረግ ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባታል። በዚሁ ምድብ ፈረንሳይ ከኢራቅ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ በፊላደልፊያ ስታዲየም ይጫወታሉ። የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት ያገኘችው ፈረንሳይ ድል ከቀናት ወደ ጥሎ ማለፉ ትገባለች። ኢራቅ በውድድሩ ላይ ለመቆየት ከጠንካራዋ ፈረንሳይ ሶስት ነጥብ ማግኘት ይጠበቅባታል። በምድብ 10 ጆርዳን ከአልጄሪያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ በሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤሪያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታቸው ጆርዳን በኦስትሪያ 3 ለ 1፣ አልጄሪያ በአርጀንቲና የ3 ለ 0 ሽንፈት አስተናግደዋል። ሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ ይፋለማሉ። አሸናፊው ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ተስፋውን ያለመልማል። በዚሁ ምድብ አርጀንቲና ከኦስትሪያ ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ በዳላስ ስታዲየም ይጫወታሉ። የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ያሸነፉት ሁለት ሀገራት የሚያደርጉት ጨዋታ ትኩረትን ስቧል። ጨዋታውን የሚያሸንፈው ሀገር ወደ ጥሎ ማለፍ መግባቱን ያረጋግጣል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
Jun 22, 2026 52
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ትናንት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እስከ 90ኛው ደቂቃ ተደርጎ በመብራት ምክንያት መቋረጡ ይታወቃል። የቡድኖቹ ቀሪ ስድስት ደቂቃ ዛሬ ረፋድ ላይ የተካሄደ ሲሆን ጨዋታው ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ከሶስት ተከታታይ ድሎች በኋላ አቻ የወጣው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ50 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ከፍ አድርጓል። ምድረ ገነት ሽሬ በ39 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ከአውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ እጅ ወጥቶ የማያውቀው የዓለም ዋንጫ ክብር
Jun 22, 2026 95
በሙሴ መለሰ እግር ኳስ በዓለም ላይ ተወዳጅ ከሆኑ ስፖርቶች መካከል አንዱ ነው። በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ትኩረት የሚስብ ግዙፍ ውድድር መሆኑ ይታወቃል። የዓለም ዋንጫ ትልቁ ስፖርታዊ ሁነት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ ግዙፍ ሁነት መካሄድ ከጀመረ አንድ ክፍለ ዘመን ሊያስቆጥር ነው። እ.አ.አ በ1930 የመጀመሪያው ዓለም ዋንጫ ኡራጓይ አስተናጋጅነት ተከናውኗል። በወቅቱ አዘጋጇ ሀገር አርጀንቲናን በመርታት ታሪካዊውን ዋንጫ አንስታለች። እስከ አሁን በተደረጉ 22 የዓለም ዋንጫዎች 80 ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህ ውሰጥ ዋንጫ ማንሳት የቻሉት ስምንት ሀገራት ብቻ ናቸው። ብራዚል፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ አርጀንቲና፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ፣ እንግሊዝ እና ስፔን ዋንጫውን ያነሱ ሀገራት ናቸው። በውድድሩ የ96 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ዋንጫው ከአውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ ሀገራት እጅ ወጥቶ አያውቅም። ከዚህም ባለፈ በነዚህ አህጉራት ከሚገኙ ሀገራት ውጪ ለፍጻሜ አልፎ የሚያልቅ ብሔራዊ ቡድን አለመኖሩ ሌላኛው ትኩረት የሚስብ ጉዳይ ነው። ከ22ቱ የዓለም ዋንጫዎች 12ቱ ወደ አውሮፓ ሀገራት አምርተዋል። የደቡብ አሜሪካ ሀገራት 10 ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል። ብራዚል አምስት ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ስኬታማዋ ሀገር ናት። ጀርመን እና ጣልያን በተመሳሳይ አራት ጊዜ ውድድሩን በማሸነፍ ይከተላሉ። አርጀንቲና ሶስት ጊዜ ዋንጫውን ማንሳት ችላለች። የወቅቱም የውድድሩ አሸናፊ ናት። ፈረንሳይ እና ኡራጓይ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን አንስተዋል። እንግሊዝ እና ስፔን በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል። በዓለም ዋንጫው ከሰባት አህጉራት የተወጣጡ ሀገራት እየተሳተፉ ቢገኝም አሸናፊነቱ ከአውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ አለመውጣቱ የሁለቱን አህጉራት ፍጹም የበላይነት የሚያሳይ ነው። 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ጣምራ አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት እየተሳተፉ ይገኛል። በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ከደቡብ አሜሪካ እና አውሮፓ ሀገራት ወጥቶ የሌላ አህጉር ቡድን ያሸነፍ ይሆን? የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ዛሬ ይጠናቀቃል
Jun 22, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከአርባምንጭ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ። በ35ኛው ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 የረታው ፋሲል ከነማ በ49 ነጥብ ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ 20ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል አስመዝግቧል። ጨዋታው ፋሲል ከነማ በድል ጉዞው ለመቀጠል አርባምንጭ ከተማ ከመውረድ ለመትረፍ እያደረገው ባለው ጉዞ ሶስት ነጥብ ለማግኘት የሚያደርጉት ነው። በሌላኛው መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጫወታሉ። ወላይታ ድቻ በ47 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ተጋጣሚው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በተመሳሳይ 47 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በ35ኛ ሳምንት ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 ያሸነፈው ወላይታ ድቻ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። በአንጻሩ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የድልን መንገድን ለማግኘት ይፋለማል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሀዲያ ሆሳዕና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች አቻ የተለያየው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ42 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል። ሀዲያ ሆሳዕና በ43 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ካለፉት ሶስት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻለም። ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚጫወቱ ሲሆን ሶስት ነጥብ የሚያገኘው ቡድን በሊጉ መቆየቱን የሚያረጋግጥበት እድል ሊኖር ይችላል። በተያያዘም ትናንት በመብራት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽሬ መርሐ ግብር ቀሪ ስድስት ደቂቃ ከረፋዱ አራት ሰዓት አንስቶ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታው እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ግብ አልተቆጠረም።
አካባቢ ጥበቃ
በነቀምቴ ከተማ ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተዘጋጅተዋል
Jun 22, 2026 50
ነቀምቴ፤ ሰኔ 15/2018 (ኢዜአ)፦በነቀምቴ ከተማ ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መዘጋጀታቸውን የከተማው ግብርና ፅህፈት ቤት ገለጸ። የነቀምቴ ከተማ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ከድር፤ በከተማዋ ዘንድሮ ለምግብነት፣ ለአፈር ለምነት፣ ለከተማ ውበትና ለደን ልማት የሚውሉ 790 ሺህ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። በከተማው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተጀመረ ወዲህ በተተከሉ ችግኞች ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን ኃላፊው ገልጸዋል። በዚህም የተራቆቱ መሬቶችን በዕፅዋት ለመሸፈን፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም የኅብረተሰቡን ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ባህል ለማጠናከር ተችሏል ብለዋል። የታቀደውን ግብ ለማሳካትም በግል፣ በመንግሥት እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት በሚንቀሳቀሱ 13 የችግኝ ጣቢያዎች ውስጥ ችግኞቹ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። የዘንድሮው የችግኝ ተከላ በ15 ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ በዚሁ መሬት ላይ ከ700 ሺህ በላይ የችግኝ መትከያ ጉድጓዶች ዝግጅት መጠናቀቁን ጠቁመዋል። በከተማዋ 65 ሺህ ነዋሪዎች በችግኝ ተከላው ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ተከላው በይፋ መጀመሩን አንስተዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ የአየር ንብረት ሚዛንን ከመጠበቅ ባለፈ፣ እስካሁን ከ150 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረጉንም ኃላፊው ጠቅሰዋል። የከተማዋ የጨለለቂ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አበበ ኢድሪስ፣ ለአመታት በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ሲሳተፉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ከራሳቸው አልፈው ልጆቻቸው ዛፍ የመትከል ባህል እንዲያዳብሩና የተተከሉትን እንዲንከባከቡ የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። የበኬጀማ ቀበሌ ነዋሪ አቶ እውነቱ ኃይለየሱስ በበኩላቸው፣ በየዓመቱ በችግኝ ተከላው ላይ አሻራቸውን በማኖር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በተለይም ችግኝ መትከል ብቻ በቂ እንዳልሆነ የገለጹት አቶ እውነቱ፣ የመንከባከብ ሥራም በዚያው ልክ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ በመሆኑ በከተማዋ ተጨባጭ ለውጥ እየታየ ነው ብለዋል። በዚህም ዝናብ ጊዜውን ጠብቆ እንዲዘንብ፣ ወንዞችና የደረቁ ኩሬዎች እንዲሞሉ እንዲሁም አካባቢው ከቀድሞው ይበልጥ ለምና አረንጓዴ እንዲላበስ ማገዙን ጨምረው ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት የጎርፍ ተጋላጭነትን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Jun 21, 2026 472
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018(ኢዜአ)፦ የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ። በመዲናዋ የተገነቡት የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር የልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት እና ዘመናዊነት በማሳደግ አዲስ አበባን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እያስቻሉ ነው። የኮሪደር ልማቱና የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ቀደም ሲል የወንዝ ዳርቻዎችን ተገን በማድረግ በአስቸጋሪና ለሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ በርካታ ነዋሪችንም መታደግ አስችሏል። በእነዚህ የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በተለይ በክረምት ወቅት ያጋጥም የነበረውን የጎርፍ ስጋት በመቅረፍ ነዋሪዎች ያለ ስጋት እንዲኖሩ እያስቻለ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ምክትል ኮሚሽነር ደሳለኝ ፉፋ ለአዜአ እንደገለፁት፤ በክረምት ወቅት የሚከሰተውን የጎርፍና አደጋ ለመከላከል ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ኮሚሽኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን፣ በከተማዋ የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች እና የጎርፍ መውረጃዎች በቆሻሻ እንዳይደፈኑ የማጽዳትና የመጠገን ስራዎችን በትኩረት እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ነዋሪዎች በወንዞችና በፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች ላይ ቆሻሻ እንዳይጥሉ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል። የጎርፍ ተጋላጭ ቦታዎች ተለይተው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የመከላከል እርምጃዎችን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። የወንዝ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ስራዎች የውሃ ማስወገጃ ቱቦዎችን ችግር በመፍታት በክረምቱ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎርፍ አደጋ ስጋቶችን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል። ይህም ለከተማው ነዋሪ እፎይታን የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ በአረንጓዴ ዐሻራና በኮሪደር ልማት በምሳሌነት የምትጠቀስ የአፍሪካ ከተማ ሆናለች- አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር
Jun 21, 2026 269
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018(ኢዜአ)፦አዲስ አበባ በአረንጓዴ ዐሻራና በኮሪደር ልማት ባከናወነቻቸው አስደናቂ ተግባራት በምሳሌነት የምትጠቀስ የአፍሪካ ከተማ ሆናለች ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ‘‘ተስፋን እንትከል’’ በሚል መሪ ሀሳብ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምሯል። በመርሃ ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ዘንድሮ የምናከናውነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ በሆነ መንገድ ባከናወንንበት ማግስት መጀመሩ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው እንደሆነ ገልጸዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተከናወኑ ሥራዎች ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ለዘላቂ ልማት አይተኬ ሚና እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የተሠራው ታላቅ ሥራ ዓለም አቀፍ እውቅናን ማስገኘቱን ገልጸዋል። የአካባቢ ጥበቃ ሥራ በመንግሥት በተሰጠው ቀዳሚ ትኩረት በተቋም እየተመራ መሆኑ ሥራውን ይበልጥ ስኬታማና ውጤታማ እንዳደረገው አብራርተዋል። አዲስ አበባ ከተማም በአረንጓዴ ልማትና በኮሪደር ልማት ባከናወነቻቸው አስደናቂ ተግባራት በአፍሪካ ደረጃ በምሳሌነት የምትጠቀስ ከተማ እየሆነች መምጣቷን ገልጸዋል። ሁሉም ዜጋ የተጀመረውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በላቀ ተነሳሽነት በመቀላቀል ለሀገር ዘላቂ ልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትም ጥሪ አቅርበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሀገር አቀፉ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በመዲናዋም ላለፉት ዓመታት ሁሉም ህብረተሰብ በተደራጀ አግባብ እየተሳተፈበት በስኬታማነት ተተግብሯል። ባለፉት የመርሃ ግበሩ የትግበራ ዓመታት በአዲስ አበባ 90 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፥ ይህም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የምትመች ከተማ እንድትሆን እያስቻለ ነው ብለዋል። የከተማዋ የአረንጓዴ ሽፋንም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን መስፈርት ለማሟላት በዕድገት ጉዞ ላይ መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፥ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 2 ነጥብ 8 በመቶ አሁን ላይ ወደ 24 በመቶ ማደጉን ገልጸዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል። ዘንድሮና በቀጣይ ዓመት በሚተከሉ ችግኞች የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። የምንተክለው ተስፋችንን፣ ራዕያችንን እና ምግባችንን ነው ያሉት ከንቲባዋ ዛሬ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ ችግኞችን የምንተክለው ነገ የተሻለችና ብልጽግናዋ የተረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመገንባት መሆኑን አስገንዝበዋል። ፅዱ፣ ውብና አረንጓዴ ከተማ ለመገንባት ከመትከል ባሻገር የተተከሉ ችግኞችን በየጊዜው መንከባከብና መጠበቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያበረከቱ መሆኑን ተናግረዋል። የከተማዋን ሥርዓተ ምህዳር በመጠበቅና የአረንጓዴ ሽፋኗን በማሳደግ ረገድ የሕዝቡ ተሳትፎ የላቀ ነው ብለዋል። በዘንድሮው ዓመትም በየአካባቢው ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ ሥራን በልዩ ትኩረት ማከናወን ከሁሉም እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች ተዘጋጅተዋል
Jun 21, 2026 377
አሶሳ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በአቡራሞ እና ኡራ ወረዳዎች የሚገኙ የችግኝ ጣቢያዎችን በመጎብኘት ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ዝግጁ የሆኑ ችግኞችን ተመልክተዋል። የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚመጡ ጫናዎችን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም ከመፍጠሩም በላይ፣ የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እየተሰሩ ካሉ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎች መካከል ቀዳሚው ነው። አርሶ አደሩ ከዘርፉ የሚያገኘውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በመገንዘብ በየዓመቱ በርካታ ችግኞችን እየተከለ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው፤ በዘንድሮው መርሃግብርም ለምግብ ዋስትና የሚሆኑ የኢኮኖሚ፣ የደን እና ልዩ ልዩ ጠቃሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል። በተለይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት በመስጠት ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን የሚችሉ፣ ዝርያቸው የተሻሻሉ የፍራፍሬ ችግኞች በብዛት መዘጋጀታቸውንም ኃላፊው አክለው ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓትም የቦታ ልየታ እና የጉድጓድ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሆነ ጠቁመው ሰኔ 16 ቀን 2018ዓ.ም በክልል ደረጃ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የአቡራሞ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ በበኩላቸው፤ በወረዳው በሚገኙ ከ11 በላይ የችግኝ ጣቢያዎች ከ13 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ችግኞችን በክላስተር በመትከል የአፈር መሸርሸርን እንዲከላከሉ እና ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ እንዲሰጡ ይደረጋል ነው ያሉት። በተመሳሳይ በኡራ ወረዳ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን የተናገሩት ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ኃላፊ አቶ ታጀዲን ሙሐመድ ናቸው። ከመንግስት በተጨማሪ ግለሰቦች በማህበር ተደራጅተው ችግኝ በማዘጋጀት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውንም አቶ ታጀዲን አስረድተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 10654
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 7979
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 6799
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 6701
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
Jun 21, 2026 456
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 14/2018 (ኢዜአ) ፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? በሳምንቱ ቢሾፍቱ አዲሱ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአዲስ አበባ 40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከባሕር ጠለል በላይ በ1 ሺህ 910 ሜትር ከፍታ ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ ግንባታው በመከናወን ላይ ይገኛል። የኤርፖርቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚያስችል ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የቢሾፍቱ ኢርፖርት ኢትዮጵያን ከዓለም ቀዳሚ የአቪዬሽን ማዕከላት ተርታ ለማሰለፍ የሚያስችል ታሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ሳምንት ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በስፍራው በመገኘት የግንባታውን ሂደት የተመለከቱ ሲሆን ግንባታውን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅም ሌሊትና ቀን በከፍተኛ ጥረት እየተገነባ ይገኛል ብለዋል። በእለቱም የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በቢሾፍቱ ያስጀመሩ ሲሆን ዘንድሮ የተያዘውን የ8 ቢሊዮን ችግኞች የመትከል ግብ ለማሳካት በሚደረገው ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ በመገኘት የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነበር። በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክትም ሀገራችንን በጋራ ማንሳት የምንችለው አንዳችን ለሌላችን እጃችንን ስንዘረጋ ብቻ ነው! ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በዚህ ሥራ እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል። የሀገር መከታና የህዝብ አለኝታ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህዝብ ወገንተኝነቱንና እና አለኝታነቱን በተግባር ማሳየቱን ቀጥሎበታል። ሰራዊቱ በጦር ሜዳ ጠላትን ድል ከመንሳት ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ የሚወጣ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን አሳይቷል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት 403ኛ መከታ ኮር የተመሰረተበትን 4ኛ ዓመት በዓል በተለያዩ ተላላቅ መርሃ ግብሮች ባከበረበት ወቅት በሰሜን ጎንደር ዞን የ"ጭና ሰማዕታት መታሰቢያ ጤና ጣቢያ" ገንብቶ ለአካባቢው ማህበረሰብ አስረክቧል። በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የሰራዊቱ የጀግንነት ታሪክ እንደ ውቅያኖስ የማይነጥፍ ከመሆኑም በላይ፣ በጭና ግንባር የተቀዳጀው ድል የጠላትን ፖለቲካዊና ወታደራዊ አቅም ሙሉ በሙሉ የሰበረ የድል ማህተም ነው ብለዋል። ለልማት- የሃይል አማራጭን ማስፋት በኢትዮጵያ ከከተማ እስከ ገጠር የተሰናሰለ የሃይል ልማትን በማስፋት አማራጭ የሃይል አቅርቦት ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ሳምንትም በሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ ከ312 ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት የሚያስችል የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሡልጣን ወሊ (ዶ/ር)፤ በኢትዮጵያ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጥረት በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ለዘላቂ ልማትና ለዜጎች ተጠቃሚነት የሃይል አማራጭን የማስፋት ስራ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን አንስተዋል። በምርታማነት የምግብ ስርዓት ችግርን መፍታት በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ችግርን ለመፍታት እስከ ታችኛው መንግስታዊ መዋቅር ድረስ የሚዘልቁ የተለያዩ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዚሁ መሰረትም በምግብ ስርዓት አለመስተካከል የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገልጿል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በክልሉ ስርዓት ምግብ ሽግግርና የቀዳማዊ ልጅነት ልማት ፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄዷል። የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈች ምርምር ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ሥራዎችና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጸውም በዚህ ሳምንት ነው። በዩኒቨርሲቲው በምርምር ፕሮጀክቶች እና በማህበረሰብ አገልግሎቶች የተከናወኑ ተግባራትን ለመገምግምና ቅንጅታዊ ሥራን ለማጠናከር ያለመ መድረክም አካሄዶ ነበር። መድረኩ በተለይ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን እውን ለማድረግና ዓለም አቀፍ ዕድሎችን አስፍቶ ለመጠቀም የተመራማሪዎችን አቅም ማሳደግ ላይ አተኩሮ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ 54 የምርምር ሥራዎችን እንዲሁም 70 የማህበረሰብ አገልግሎቶችን ማከናወኑን ጠቁመዋል። በቀብሪ በያህ ከተማ የወጣቶች የልማት ተጠቃሚነት በሶማሌ ክልል የልማትና የምርታማነት አጀንዳዎች በውጤታማነት ቀጥለዋል። የወጣችንና አጠቃላይ የክልሉን ህዝብ የልማት ፍላጎት መሰረት አድርገው እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው። በዚሁ መሰረት በክልሉ ፋፈን ዞን ቀብሪ በያህ ከተማ በማህበር ተደራጅተው ሥራ የፈጠሩ ወጣቶች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል። አብዲከሪን መሀመድ እና ጓደኞቹ በማህበር ተደራጅተው በዶሮ እርባታ በመሰማራት በሌማት ትሩፋት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል። ሥራውን ከጀመሩ ወዲህ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ ለሌሎች ወገኖችም ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ይናገራሉ። እንደ አጠቃላይ በሶማሌ ክልል ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ቀጥለዋል። የበጀት ክለሳ በዚሁ ሳምንት የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ2018 የበጀት ዓመት የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የቀረበለት የበጀት ክለሳ አፅድቋል። ካቢኔው በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አማካኝነት የቀረበለትን ከ301 ሚሊየን 693 ሺህ 178 ብር የበጀት ክለሳ ነው ተወያይቶ ያፀደቀው። የበጀት ክለሳው በተለይም የፊስካልና ፋይናንሻል አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸውና የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች የሚውል ነው ተብሏል። የአንድ ማዕከል አገልግሎት ኢትዮጵያ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮቿን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ልትሰጠው እየተጋች ነው። ለዚህ ዋና ማሳያው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ነው። ማዕከሉ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ይገኛል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኮንታ ዞን የተገነባውን ኮንታ መሶብ የአንድ ማዕከል መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል በተበታተነ ሁኔታ ይሰጡ የነበሩ የመንግሥትና የማኅበራዊ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማሰባሰብ ለዜጎች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው። የኮንታ ማዕከልም ሕዝቡ ከቢሮ ወደ ቢሮ በመዘዋወር የሚያጠፋውን ጊዜ፣ ወጪና እንግልት በእጅጉ በመቀነስ ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛቸዋል ተብሏል። የስደተኞች መጠጊያ- ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች መጠጊያ የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኡራ ወረዳ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተከብሯል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ክልሉ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞችን ከመቀበል ባለፈ ስደተኞችን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በክልሉ አራት መጠለያ ጣቢያዎች ላይ ከ112 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ገልፀው፥ ስደተኞች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ መስተጋብር በመፍጠር በአብሮነት እየኖሩ ነው ብለዋል። ስደተኞች የውሃ፣ የትምህርት የጤናና ሌሎች የመሠረተ ልማቶችን ከተቀባዩ ማህበረሰብ እኩል ተጠቃሚ መሆናቸው የኢትዮጵያን ስደተኞች አያያዝ የተሻለ ተሞክሮ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ጋምቤላ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት በመጪው የህዝብ ውክልና ስራ ስምሪት ወቅት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በተመለከተ የኦሬንቴሽን ፕሮግራም አካሂዷል። የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋል፣ የህዝብ ውክልና ተግባር የምክር ቤት አባላት ዋና ሃላፊነት መሆኑን ገልፀው፣ አባላቱ ወደ ህዝቡ በመቅረብ የህብረተሰቡን ፍላጎት፣ ችግርና አስተያየት በአግባቡ በማሰባሰብ ለመንግስት አካላት ማድረስ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ምክትል አፈ ጉባኤው እንዳሉት፣ የህዝብ ውክልና ስራ በዜጎችና በምክር ቤቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የህዝብ ተሳትፎን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ አባላቱ በተሰጣቸው ኃላፊነት ትጋትና ቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስበዋል። ድሬደዋ ድሬደዋ የመስኖ ግንባታ። 'በቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም' በሁላሁሉል ገጠር ቀበሌ ውስጥ የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም የተሰሩ የንፁህ መጠጥ ውሃና የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች፥ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብረሃም በላይ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል። የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስትር አብረሃም በላይ (ዶ/ር) እና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ ግድቡን በመረቁበት ወቅት ከምንም በላይ ለሰው ልጆች ህይወት እጅግ አስፈላጊ የሆነውና፥ የአስተዳደራችን የገጠር ነዋሪ ህብረተሰብ መሠረታዊ ፍላጎትና የረጅም ዘመናት ምኞት የነበረውን፥ የውሃ ጥያቄ በጋራ ርብርብ መመለስ መቻል የሚሰጠው ደስታ እጅግ ልዩ ነው ብለዋል ከንቲባው። የድሬዳዋን ማህበረሰብ የምግብ ሉኣላዊነት የማረጋገጥ፣ አርሶአደሩ ነዋሪ ከራሱ አልፎ ለገበያ በማቅረብ ኑሮውን እንዲያሻሽል እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የመስኖ ልማት ሥራዎችን እንዲያከናውን በማገዝ ረገድ ቀጣይነት ያለው ስራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። አፋር ሳምንቱ በአፋር ክልል በማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ያሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ወጣቶች፣ ባህልና ስፖርት ቢሮ ያስታወቀበትም ነበር። የአፋር ክልል አብዛኛው ማህበረሰብ ከፊል አርብቶ አደርና አርብቶ አደር በመሆኑ፣ በየዓመቱ የሚከናወኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶች ለመሙላት ትልቅ ሚና አላቸው። በተለይም የአየር ንብረት መለዋወጥ፣ የውሃ እጥረት እና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን ተቋቁሞ ዘላቂ ልማት ለማምጣት የወጣቶችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ አቅም ወሳኝ ግብዓት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። ማጠቃለያ ሳምንቱ በሁሉም ክልሎች መደበኛ የልማት፣ የማህበራዊ እና የሰላም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው የቀጠሉበትም ነበር። በሁሉም ክልሎች የስድስተኛ እና ስምንተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተካሄዷል። በተመሳሳይ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ችግኝ ዝግጅት በሁሉም ክልሎች እየተከናወነ ይገኛል።
የክልሎች ቅኝት- በወፍ በረር
Jun 15, 2026 2494
በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም ባሳለፍነው ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? 👉የተራሮች ስር ፈርጥ - ወልዲያ የዛሬው የወፍ በረር ምልከታችን የሚጀምረው የተራሮች ስር ፈርጥ በሆነችው ወልዲያ ከተማ በመገኘት ነው። ከደሴ በ120 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውና በረጃጅም ተራሮች የተከበበችው ወልዲያ ከተማ ከነበረችበት ጉስቁልና ወጥታ አሁን ላይ በውበት ፈክታ ትገኛለች። በሳምንቱ በዚህች ከተማ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ የኮሪደር ልማቷንና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀዋል፤ ተዘዋውረውም ጎብኝተዋል። በተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ትውፊቶች ስሟ ጎልቶ የሚጠራው ወልዲያ እንደ ከዋክብት ፈክታ እንግዶቿን ተቀብላ አስተናግዳለች። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ወደ ገጠር ጭምር እየተስፋፉ መሆኑን አንስተው በቀጣይ ኢትዮጵያ ዕዳዎቿን እያራገፈች ተስፋዎቿን እየጨበጠች ትገሰግሳለች ብለዋል። 👉የሸደር አዳሪ ትምህርት ቤት የሚቀጥለው መዳረሻችን በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን አውበሬ ወረዳ ሼደር ከተማ አዲስ የተገነባውን አዳሪ ትምህርት ቤት መመረቅ ይሆኗል። የትምህርት ቤቱን ግንባታ መርቀው ስራ ያስጀመሩት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ናቸው። ርዕሰ መስተዳድሩ በመልእክታቸው፤ በክልሉ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማስፋት የተማረ ትውልድ ማፍራት የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። በ138 ሚሊየን ብር የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ስራ መጀመሩ ለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን አንስተዋል። 👉የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የበረራ ቅኝታችን ቀጥሎ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቂምቢቢት ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለ የስንዴ ምርት የመጎብኘት እድል አግኝተናል። በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ቂምቢቢት ወረዳ በ21 ሺህ 463 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የመስኖ ስንዴ ሰብል መሰብሰብ ተጀምሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ በክልሉ እየተከናወነ የሚገኘው የበጋ መስኖ ልማት ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር እንዲሁም የአርሶ አደሩን ገቢ እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት እያሳደገ ይገኛል ብለዋል። የግብርና ሜካናይዜሽንን በስፋት በመጠቀም እንዲሁም ፈጠራን በማከል ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረቱ በተሳካ መልኩ መቀጠሉን አንስተዋል። 👉ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ዓለም አቀፍ ክስተት ነው። ችግሩ በተለይም በታዳጊ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብአዊ ጉዳቶችን እያስከተለ ይገኛል። ኢትዮጵያም የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደመሆኗ መጠን ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ መፍትሄ ለመስጠት ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች። በዚህ ረገድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ፍልሰትን ለመግታት በሚከናወኑ ሥራዎች በምርምር እያገዙ ናቸው። በሂደቱ ውጤታማነት ላይ የሚመክር መድረክ በሰመራ በተደረገበት ወቅት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲዎች የሕግና ማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲኖች ችግሩን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በምርምርና በማማከር እያገዙ መሆናቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሰዎች ህገወጥ ዝውውርንና ፍልሰትን ለመግታት የነፃ የሕግ ድጋፍና የማማከር አገልግሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን ለህብረተሰቡ እየሰጡ ናቸው። 👉የኢትዮጵያ እያመረተች ነው በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር «ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት» በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል። መርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እና ሌሎችም በተገኙበት ተካሂዷል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የገቢ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ ለውጭ ምንዛሬ አይነተኛ የገቢ ምንጭ መሆን አስችሏል ብለዋል። 👉መሶብ በአርባ ምንጭ፣ ዲላ እና ነቀምቴ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተስፋፋ የመጣው የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት በዚህ ሳምንት አርባ ምንጭ፣ እና ዲላ ከተሞች ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። የመሶብ ማእከላቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀዋል። የዲጅታል አሰራርን በማስፋት ለዜጎች ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት የመስጠት ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል። በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። 👉ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በኢፌዴሪ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሠረት፣ በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች እና የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር በተለያዩ ግንባሮችና ካምፖች የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በመደበኛው የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ለመስጠት የሚቸገሩ ስለመሆኑ ያነሳል። በመሆኑም ይህን መሠረታዊ መብት ለማስከበርና የምርጫውን አካታችነት ለማረጋገጥ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ መመሪያዎችን በማውጣት ልዩ የምርጫ ጣቢያዎችን አደራጅቷል። በመሆኑም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በእለቱ ድምፅ መስጠት ካልቻሉት መካከል የሰሜን ምስራቅ ዕዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ከቀናት በፊት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በተመሳሳይ በአፋር ክልል እና በደብረ ብርሃን ከተማ በጊዜያዊ መጠለያዎች የሚገኙ ዜጎች በልዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል። 👉የመኸር እርሻ ንቅናቄ በሲዳማ ክልል የመኸር እርሻን በንቅናቄ በመምራት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡና ገበያን የሚያረጋጉ የግብርና ልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በንቅናቄ መድረኩ ርእሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት መሬት ጦሙን እንዳያድርና ግብአትን በወቅቱ በማቅረብ እንዲሁም ለግብርና ቴክኖሎጂ ትኩረት በመስጠት ምርታማነቱን ማሳካት አስችሏል። ዘንድሮም ተግባሩን በማስቀጠል የበልግ ሰብልን ከመሰብሰብ ጎን ለጎን የመኸር እርሻን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት መሰጠቱ በዘገባው ተመላክቷል። ይህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ትርፍ በማምረት ገበያን ለማረጋጋትና ለኢንደስትሪዎች ግብአት ለማቅረብ ያስችላል ነው የተባለው። በምርት ዘመኑ የተያዘውን እቅድ ለማሳካትም አመራሩ ህብረተሰቡን በማስተባበር ለውጤቱ መትጋት እንዳለበትም በውይይቱ ተነስቷል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የምርጥ ዘር ብዜትን በዓይነት፣ በመጠንና በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ማቅረብ ተችሏል። ቢሮው በግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ እና በክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘር ብዜት ዕቅድ አፈጻጸምና ዝግጅት ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የግብርና ግብዓትና ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ እንደገለጹት፤ በክልሉ የምርጥ ዘርን በጥራትና በመጠን ለአርሶ አደሩ በወቅቱ በማድረስ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል። ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ለኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓትን ለማቅረብና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አግዟል። ተግባሩን በማስቀጠልም በ2017/18 የምርት ዘመን በክልሉ ከ2 ሺህ 200 ሄክታር በላይ መሬት ላይ ከ30 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ማምረት መቻሉንም ገልጸዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት
Jun 14, 2026 1856
በኢዜአ ዐይን …! በሙሴ መለሰ አረንጓዴ ዐሻራ - ለዓየር ንብረት ለውጥ ላለመበገር የሚደረግ ትጋት የዓየር ንብረት ለውጥ የምድራችን ፈተና ነው። ልብ መባል ያለበት ግን አፍሪካ ለዓየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዋ አነስተኛ ሆኖ ሳለ ጉዳቷ ከፍተኛ መሆኑ ነው። ስለዚህ አኅጉሪቱ ዕጇን አጣጥፋ ወቃሽና ጠባቂ ከመሆን ይልቅ፤ በፈተና ውስጥ ሆናም በዘላቂነት የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ለማምጣት መትጋት አለባት። የሩቅ መፍትሔ አይጨበጥም፤ አይዘልቅምና። ከመፍትሔዎች አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ነው።በዚህ ሂደት ደግሞ የኢትዮጵያ ድንቅ ስራ የሚወደስ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት፤ በ2011 ዓ.ም በተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር እስካሁን ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ለዓየር ንብረት ለውጥ ከተሰጡ ምላሾች መካከል በፊትአውራሪነት ይጠቀሳል። መርሐ-ግብሩ የጋራ ነው በሚል ዕሳቤ በርካቶችን በንቃት አሳትፎ ለዓለም የሚደርስ የዓየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ማምጣት እንደሚቻል በተግባር ዐሳይቷል። የደን ሽፋን መጠንን አሳድጓል። ይህም በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ የራሱን ሚና እያበረከተ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአረንጓዴ ዐሻራ ሚና ልቆ ይነሳል። ይህም የተራቆተ መሬትን ወደ ነበረበት ከመመለስ፣ የውኃ ሀብት አሥተዳደርን ምቹ ከማድረግ እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ነው። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብሩ በዕድሜ፣ በጾታ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በሥራ ዘርፎች፣ በኑሮ ደረጃ፣ በሐይማኖት ሳትለይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲሳተፉበት በማድረጓ በዘርፉ ስኬታማ ጉዞ ላይ ናት። ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀት ከመሆን አልፎ ለጎረቤቶቿ ችግኝ በመለገስ መርሐ-ግብሩ እንዲስፋፋ እየተጋችም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ሲናገሩ፤ አረንጓዴ ዐሻራ ኢትዮጵያ ትላልቅ ነገር አስባ፣ ትላልቅ ነገር ተልማ፣ ትላልቅ ነገር አቅዳ እና ሕዝቦቿን አስተባብራ ማሳካት እንደምትችል ለሌሎቹ ማሳያ ነው ማለታቸውም ከላይ ያነሳነውን ሐሳብ ያዳብረዋል። በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ በልዩ ትኩረት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሳይቆራረጥ እየተሠራ መሆኑን፤ በየዓመቱም በሚተከሉ ችግኞች ብዛት፣ በሚተከልበት መሬት ስፋት እና በሚሳተፉ ታታሪዎች ቁጥር እያደገ መሆኑን ያመላክታል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች እየወጡ በችግኝ ተከላ መሳተፋቸው የሀገርን የጋራ ራዕይ ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል። #አረንጓዴ_ዐሻራ #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 6727
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ትንታኔዎች
የጡት ካንሰርን ለመከላከል …
Jun 16, 2026 2681
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው የጡት ካንሰርን ለመከላከል … ለጡት ካንሰር ላለመጋለጥ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ስለ አጋላጭ ምክንያቶቹ እንዲሁም ምልክቶቹና ሕክምናው የካንሰር ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ቢኒያም ተፈራ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ - ካንሰር እንዴት ይከሰታል? እንደ ዶክተር ቢኒያም ገለጻ፤ ጤናማ የሰው ልጅ በሕይዎት ዑደት ሲያልፍ በሰውነቱ ውስጥ ያሉ ኅዋሶች (ሴሎች) በመደበኛ ሁኔታ ይራባሉ፤ ጊዜያቸውን ጠብቀውም ይሞታሉ። ይህን ሂደት በተፈጥሮ መቆጣጠር የሚቻልና የራሱ የሆነ የመቆጣጠሪያ መንገድ ያለው መሆኑንም ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ በአንዳንድ ምክንያቶች (በዘረመል ለውጥ ወይም በአካባቢያዊ ጉዳዮች ሊሆን ይችላል)፤ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ መራባት ሲጀምሩና ወይም መሞት ባለባቸው ጊዜ ሳይሞቱ ሲቀሩ፣ በራሳቸው አካባቢ ከመጠን በላይ በማደግ እንደ ዕጢ ያለ ነገር ሲፈጥሩ፤ ከዚህ አልፎ በአካባቢያቸው ያሉ ኦርጋኖችን መያዝ ሲጀምሩ እንዲሁም ወደ ሌላ የሰውነት አካል በመሄድ ባልተፈቀደላቸው ቦታ ላይ ማደግና ያለቁጥጥር መራባት የሚጀምሩበት ሂደት ካንሰር ተብሎ ይጠራል። ካንሰር ስሙ የሚሰየመው እንደተከሰተበት የሰውነት ክፍል መሆኑን አስገንዝበው፤ የጡት ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር፣ የቆዳ ካንሰር … እየተባለ የሚጠራው በዚሁ አግባብ መሆኑን አስረድተዋል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድናቸው? እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ቨርቹዋል ኦቲዝም የጡት ካንሰር ምልክቶች በጡት ውስጥ ቀደም ሲል ያልነበረ (አዲስ) ዕብጠት መከሰት፣ የጡት ቆዳ ቀለም መለወጥ፣ ቁስለት መኖር፣ ከጡት ጫፍ ላይ መግል ወይም ደም መሰል ፈሳሽ መውጣት፣ በብብት ሥር አካባቢ የሚከሰት ዕብጠት በአብዛኛው የጡት ካንሰር ምልክቶች መሆናቸውን አብራርተዋል። እነዚህ ምልክቶች ኬዙ አድጎ መታየት ሲጀምር የሚስተዋሉ መሆናቸውን በመጠቆም፤ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ምልክቶች ሳይኖሩ የጡት ካንሰር የመያዝ ዕድል መኖሩን አመላክተዋል። ወደ ጤና ተቋም መቼ መሄድ ይመከራል? የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት፤ በአጠቃላይ አንዲት ሴት ጡቷ ላይ ቀደም ሲል ያልነበረ አዲስ ለውጥ ካለ ካንሰር ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል በመገመት ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ይጠበቅባታል። ነገር ግን ከካንሰር ጋር በተያያዘ ጥርጣሬን ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቁመው ከነዚህም አንዱ በጡት ውስጥ ዕብጠት መኖርና ዕብጠቱም ምንም ዓይነት ህመም የሌለው መሆንን ጠቅሰዋል። አክለውም እስከ 80 በመቶ የሚሆነው በዕብጠት የሚመጣ የጡት ካንሰር ህመም እንደሌለው አንስተዋል። ህመም የለውም ብሎ ዕብጠትን ችላ ማለት እንደማይገባም በመምከር። በአጠቃላይ አንዲት ሴት ከላይ የጡት ካንሰር ምልክቶች ተብለው የተዘረዘሩትን ካየች በአፋጣች ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚጠበቅባት በአጽንዖት ገልጸዋል። በተጨማሪም በአጠቃላይ ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ጡታቸውን እየዳበሱ ከወትሮው የተለየ አዲስ ምልክት መኖሩን ማየት እንዳለባቸው መክረው፤ የተለየ (አዲስ) ነገር ሲኖር ወደ ሕክምና እንዲሄዱ አሳስበዋል። የአሳሳቢነት ደረጃ የጡት ካንሰር በጣም አሳሳቢ መሆኑን የሚገልጹት ዶክተር ቢኒያም፤ ከካንሰር ዓይነቶች ሁሉ በሀገራችን በቀዳሚነት ይቀመጣል ብለዋል። በተለይም ይላሉ፤ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች 1/3ኛ (31 በመቶ ገደማ) ያህሉ የጡት ካንሰር ነው። በእርግጥ ወንድንም ሴትንም ብንደምረው በብዛትም ሆነ በሽታ በማስከተል ረገድ በአንደኝነት የሚቀመጥ ነው ይላሉ። ስለ ጡት ካንሰር ያለ ግንዛቤ በሕብረተሰቡ ዘንድ ስለ ጡት ካንሰር አጠቃላይ ሁኔታዎች ሰፊ የግንዛቤ እጥረት መኖሩን ገልጸው፤ ለአብነትም ከ2/3ኛ በላይ የሚሆነው ታማሚ ወደ ሕክምና ተቋም የሚመጣው በሽታው በጣም ሥር ከሰደደ በኋላና ችግር መፍጠር ሲጀምር መሆኑን አንስተዋል። በወቅቱ ወደ ሕክምና ተቋም የሚሄዱት ሴቶች ቁጥር በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን (ከ30 በመቶ በታች) መሆኑንም አመላክተዋል። ይህ ሁሉ የሆነው በግንዛቤ እጥረት እንደሆነ ይታመናል ብለዋል። በመንግሥታዊና በግል ተቋማት ጭምር ለአብነት የጥቅምት ወርን የጡት ካንሰር ወር አድርጎ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እየተከናወነ ቢሆንም በቂ አለመሆኑን ጠቁመዋል። በተለይም ስለጡት ካንሰር በአግባቡ አለማወቅ እንዲሁም በጡት ላይ የሚስተዋሉ ምልክቶችን ልብ አለማለት (ቀለል አድርጎ በማሰብ ሥር እንዲሰድ ዕድል መስጠት) እንዳለ አብራርተዋል። በጡት ካንሰር የሚከሰት ሞትን ከፍ ከሚያደርጉት አንዱ የግንዛቤ እጥረት እንደሆነ ይታመናል ይላሉ። በወንዶች ላይ የጡት ካንሰር በወንዶች ላይም የጡት ካንሰር ሊከሰት እንደሚችል የሚናገሩት የሕክምና ባለሙያው፤ የሚከሰትበት መጠን (ቁጥር) ግን በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ነው ያስረዱት። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ላይ ቁጥሩ በዛ ቢልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ1 በመቶ በታች መሆኑንም ገልጸዋል። ዕድሜያቸው ከፍ ባሉ ወንዶች ላይ እንደሚከሰት በመግለጽ፤ ወንዶች በጡታቸው ላይ የተለየ ምልክትና ህመም ሲሰማቸው ወደ ሕክምና መሄድ እንደሚጠበቅባቸው መክረዋል። የጡት ካንሰር በሕጻናትና አዳጊዎች ላይ አይከሰትም ብሎ መደምደም ባይቻልም፤ የመከሰት ዕድሉ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ዶክተር ቢኒያም አስረድተዋል። እዚህ ላይ ብዙም አያሳስብም ይላሉ። ዕድሜና የጡት ካንሰር በአብዛኛው የጡት ካንሰር የሚከሰተው ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ መሆኑን የሚገልጹት ዶክተር ቢኒያም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ ከፍ እንደሚል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን አብዛኛው ሕዝብ ወጣት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመው፤ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑት የጡት ካንሰር ታማሚዎች ከ30 እስከ 50 ባለው ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ስለዚህ ዕድሜያቸው ገፋ ባሉም ሆነ በወጣቶች ጡት ላይ አዲስ ህመም ሲስተዋልና ምልክት ሲታይ ቶሎ ወደ ሕክምና መሄድ እንጅ፤ ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የሚከሰት ነው ብሎ ችላ ማለት ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል። ለጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች እንደ ሕክምና ባለሙያው ማብራሪያ፤ የጡት ካንሰር እኛ ቀድመን ብንሠራባቸው ተጋላጭነትን የምንቀንስባቸው እና ከቁጥጥራችን ውጭ በሆኑ (ተፈጥሯዊ) ሁኔታዎች የምንጋለጥባቸው ጉዳዮች አሉ። ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ አልኮል መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩ (ፕሮሰስ የተደረጉ) ምግቦችን ማዘውተር፣ አትክልትና ፍራፍሬ አለመመገብ ተጋላጭነቱን እንደሚጨምሩ አንስተዋል። እነዚህን በማስተካከል ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል። በተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የዕድሜ መጨመር፣ ሴት መሆን፣ በዘረመል (በጀኔቲክ) ለውጥ (በቤተሰብ ወይም በሕይዎት አጋጣሚ ከአካባቢያዊ ሁኔታ የሚመጡ የዘር መለወጦች) ለጡት ካንሰር ሊያጋልጡ እንደሚችሉ አብራርተዋል። እነዚህን ምንም ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ መፍትሔው ምልክት (ጥርጣሬ) ሲኖር ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ ነው ይላሉ። ሕክምና እና የመዳን ተስፋ የጡት ካንሰር የመዳን ተስፋው ጥሩ መሆኑን ገልጸው፤ ይህ የሚወሰነው ግን ህመሙ እንደተገኘበት ደረጃ (ስቴጅ) ነው ይላሉ። [6/16/2026 9:29 AM] awe: በአጠቃላይ ሲታይም፤ ቶሎ ወደ ሕክምና በመሄድ የታከመ ካንሰር የመዳን ዕድሉ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ባብዛኛው የሚሰጡ የሕክምና አማራጮችም፤ ኦፕሬሽን፣ ኬሞቴራፒ፣ የጨረር ሕክምና፣ የሆርሞን ሕክምና ሲሆኑ፤ አልፎ አልፎ ደግሞ እንደሁኔታው ታርጌትድ ቴራፒ እና ሚኖቴራፒ የሚባሉ የሕክምና አማራጮች መኖራቸውን ዘርዝረዋል። የሕክምና አማራጩን የሚወስነው በሽታው የተገኘበት ደረጃ (ስቴጅ) መሆኑንም አስገንዝበዋል። ምክረ ሐሳብ ሕብረተሰቡ እንዲገነዘበው የምንፈልገው ቶሎ ከታወቀ የጡት ካንሰር ታክሞ ይድናል፤ ለዚህ ደግሞ በጡት ላይ አዲስ ነገር ሲስተዋል ቶሎ ወደ ሕክምና መሄድ አዋጭ መሆኑን ነው ብለዋል። በጡት ላይ የሚስተዋል ዕብጠትና ህመም ሁሌም ካንሰር ነው ማለት ስላልሆነ ሴቶች ሳይደናገጡ ምርመራ እንዲያደርጉ መክረው፤ የምርመራ ውጤቱ ካንሰር መሆኑን ቢያሳይ እንኳ ቶሎ ወደ ሕክምና እስከሄዱ ድረስ በቀላሉ መዳን እንደሚችል መገንዘብ እንዳለባቸውም መክረዋል። ሕብረተሰቡ በአጠቃላይ ከጡት ካንሰር ጋር በተያያዘ ከሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች መቆጠብ እንደሚገባውም ይመክራሉ። ቢያንስ ዕድሜያዋ ከ20 ዓመት በላይ የሆናት ሴት በወር አንድ ጊዜ ጡቷን በመዳበስ (ዕብጠትም ካለ እንዲታያት በመስታዎት ፊት ሆና በመመልከት) ቀደም ሲል ያልነበረ አዲስ ነገር መኖሩን መከታተል ይጠበቅባታል። ይህም ኬዙ ቢከሰት እንኳ ቶሎ ለመዳን ስለሚያግዝ ይላሉ። ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ ቢቻል በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የጡት ቅድመ ምርመራ እንዲደርጉ መክረዋል። #ኢዜአ #የጡት_ካንሰር #የጤና_ነገር
በኢዜአ ዐይን…!
Jun 15, 2026 1586
በዮሐንስ ደርበው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ • እንደ መነሻ ባሳለፍነው ወርኃ ግንቦት ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አካሂዳለች። ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መታያ፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ገቢራዊነት መገለጫ፤ ሕዝባዊ መንግሥትን አንባሪ ብሎም በሕዝባዊ ምርጫ ብቻ ወደሥልጣን የሚመጣበት መንገድ ነው። ለሀገራዊ መግባባትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታም ቁልፍ ነው። • ቅድመ ምርጫ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ባለድርሻ አካላት ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነዋል። ለአብነትም፤ የምርጫ ሕጉን ከማሻሻል ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሥርዓቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የምርጫ ትምህርትና ግንዛቤን ለማስፋት ለሚሠሩ በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጥቷል። የምርጫ ሂደትን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥም በርካታ ድርጅቶች በታዛቢነት ተመዝግበዋል። የመራጮች ምዝገባም፤ በመደበኛ የመራጮች ምዝገባ (ማኑዋል)፣ ምርጫዬ በተሰኘ የሞባይል መተግበሪያ እና በድረ ገጽ አማራጭ በመቅረቡ በርካታ መራጮችን አሳትፏል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በ24 ሬዲዮ፣ በ20 ቴሌቪዥን እና በ6 ጋዜጦች በሕዝብና በንግድ ሚዲያዎች ነጻ የአየር ሠዓት ተደልድሏል፤ ሐሳባቸውንም ተደራሽ አድርገዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት • በምርጫ ወቅት በምርጫ ካርድ ሀገር የሚመራን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ ከሥልጣኔ መገለጫዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል። የመራጮች ንቁ ተሳትፎም የሕዝቡን ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያጎለብታል። ምርጫ፤ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙ፣ ተቋማዊ አሠራሮች እንዲጠናክሩ ቁልፍ በመሆኑ ጠቅላላ ምርጫው ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡበት ነው። የሕዝቡን ትጋት አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክትም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተዓምረኛም ሕዝብ ነው፤ ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባሕል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል ብለዋል። ታሪካዊ በሆነው ዕለትም፤ የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣ የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው፣ ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣ ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣ የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣ ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣ ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤ በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳዩት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ሁሉ የሥልጡን ሕዝብ ትጋት በኋላ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ አረጋግጠዋል። ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ከማለዳው 12፡ 00 ሠዓት ጀምሮ ድምፃቸውን መስጠታቸውን አስታውቀዋል። ረጃጅም ሰልፍ የነበረባቸውን የምርጫ ጣቢያዎችም እስከ ሌሊቱ 6 ሠዓት በማራዘም መራጮች ድምፅ እንዲሰጡ መደረጉን አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ የ7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በተመለከተ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ዜጎች የመምረጥ መብታቸውን በነፃነት እና በሙሉ ፈቃዳቸው እንደተጠቀሙበትም ልዑካቸው ታዝቧል። ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተግባር አሳይተዋል፤ ያለምንም ጫና የሚፈልጉትን ፓርቲ መርጠዋል፤ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ እና በተዓማኒነት የተሞላ ሂደት ነው ብለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን መስጠታቸውን ዐይተናል ብለዋል። የምርጫ ሂደቱ በተቀናጀ መንገድ መካሄዱን፣ በምርጫ ጣቢያዎችም ነፍሰ ጡር እናቶች፣ ልጆቻቸውን የያዙ እናቶች፣ ወጣቶች እና አዛውንቶች ሳይቀሩ ከማለዳው ጀምሮ ድምጽ ሲሰጡ እንደነበር መታዘባቸውን ተናግረዋል። በሁሉም አካባቢ የድምፅ መስጠት ሒደቱ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን በመጠቆም፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የታየበት መሆኑን አስታውቀዋል። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማስፈፀም ዐቅም እያደገ መምጣቱ የታየበት ስኬታማ ምርጫ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ናቸው። ምርጫውን መታዘባቸውን በመጥቀስ፤ ምርጫው በርካታ ዜጎች የተሳተፉበት፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሂደትን የተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በምርጫው አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ዜጎች ድምጻቸውን እንደሰጡም ነው የገለጹት፡፡ ይኸውም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና ይበልጥ አካታች ተሳትፎን እያጎለበተ መምጣቱን ማሳያ ነው ብለዋል። አክለውም፤ መንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙኃንና ሌሎችም አጋር አካላት ለምርጫው ስኬታማነት ሚናቸውን መወጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ የዴሞክራሲና የፍትሕ ተቋማት እንዲጠናከሩ በትኩረት መሠራቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ቦርዱ ነፃና ገለልተኛ በመሆን የማስፈጸም ዐቅሙ እያደገ መምጣቱን በማንሳት፤ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያበረከተውን አስተዋጽኦ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡ • ድኅረ ምርጫ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ፤ የ1 ሺህ 8 የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል መግባቱን ተናግረዋል። የምርጫ ጣቢያዎች የውጤት ቆጠራ ተጠናቅቆ በምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል። ከ501ዱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች 446ቱ ወደ ማዕከል መድረሳቸውንና ቀሪዎቹ የክልል ምክር ቤቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል። በሌላ በኩል በመጠለያ ጣቢያዎችና በካምፖች የድምፅ አሰጣጥ መከናወኑን ጠቁመው፤ ውጤት የማዳመር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። #ምርጫ #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #በኢዜአ ዐይን
ከአፍሪካ ሰማይ እስከ ዓለም ከፍታ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ!
Jun 12, 2026 6727
በኢዜአ ዐይን ...! በዮሐንስ ደርበው የኢትዮጵያ የዘመናት ስኬት መገለጫ፤የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከል እና በኢንዱስትሪው በዓለም ስመጥር ተቋማት መካከል አንዱ ነው ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ። አየር መንገዱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስገባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የኢትዮጵያን ወጪ ንግድ በመደገፍ፣ኢትዮጵያን በአቪዬሽን መሠረተ-ልማት ከፍ በማድረግ፣የቱሪዝም ዘርፉን በማገዝ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው። አየር መንገዱ ወደ ካይሮ "አንድ" ብሎ የጀመረው ታሪካዊ ጉዞ ዛሬ ላይ በአምስት አኅጉራት 145 መዳረሻዎችና በ147 ዘመናዊ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያቀላጠፈም ይገኛል። አየር መንገድ የገነባው ዐቅም በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስቻሉት ሲሆን የወደፊት ዕቅድና የዐቅም ግንባታ ትኩረቶቹ ለቀጣይ ስኬቱ ቁልፍ እንደሚሆኑም ይጠበቃል። በተለያዩ ጊዜያትም ዓለም አቀፍ፣አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን መሰብሰቡ ለዚህ ሁነኛ አስረጂ ይሆናል።የበረራ አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት፤የተቋማዊ ዕድገቱን ማስቀጠል እንዳስቻለውም ይገለጻል። አየር መንገዱ በታላቅነቱ ተፎካካሪ ሆኖ ለመዝለቅ የሀገር ውስጥ አቅሙን ማሳደግ እና የነበሩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን በማደስ፣በማስፋፋት፣በማዘመን፣አዳዲስ በመገንባት ክልሎችን በአየር ትራንስፖርት በማስተሳሰር ለዜጎቹ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር በልዩ ትኩረት እየሠራ ይገኛል። በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡትን ስኬቶች በቴክኖሎጂውም ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው? በአረንጓዴ ዐሻራ ጸንቶና ተግቶ መሥራት ዘመኑ የሚፈልገው ዐርበኝነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻውን በቅርቡ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም የእዚሁ ትጋት አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።ይህ መዳረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ይህ መሠረተ-ልማትም ለአካባቢው ነዋሪ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ትልቅ ሥጦታ ነው። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ይህም የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ያነቃቃል እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል ብለዋል። የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዱ በእርግጥም “የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው ሲሉ ገልጸውታል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዳዲስ የመንገደኛ አውሮፕላን፣ የበረራ መዳረሻ በማስፋትና በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ አስደናቂ ሥራ እየሠራ ነው። በሰፊ የአውታረ መረብ መስመሮች በርካታ ሀገራትን ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ ለመሆንም በቅቷል። አየር መንገዱ መንገደኞችን ከሀገር ሀገር ከማዘዋወር፤ከፍተኛ የካርጎ አገልግሎትን ከማቀላጠፍ ባሻገርም በሀገራት መካከል ንግድን፣ቱሪዝምን፣ኢንቨስትመንትን እና ውህደትን በመፍጠር በኩል ለአመታት የዘለቀ ዝናን አትርፏል። ይህ የተለያዩ አውሮፕላን ማረፊያዎችን የመገንባት ስትራቴጂ ኢትዮጵያን የወደፊቷ የአፍሪካ ግንባር ቀደም የአየር ትራንስፖርት በር የማድረግ ዓላማን ያነገበ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን ባስጀመሩበት ወቅትም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ ታሪክ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ፕሮጀክት እንደሚሆን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህም የኢትዮጵያን ፈጣን የአየር ትራንስፖርት እድገት እና እየሰፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ትስስር ዘላቂ በማድረግ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ አዲስ ሜጋፕሮጀክት እየለማ ይገኛል ማለታቸው የዚሁ ማሳያ ነው። #በኢዜአ_ዐይን…! #ኢዜአ #የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ #Ethiopian_News_Agency
ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ምንድን ናቸው?
Jun 12, 2026 2565
የጤና ነገር … በዮሐንስ ደርበው የሰው ልጅ ሊሻሻሉ በሚችሉ እና በማይችሉ ተፈጥሯዊ ምክንያቶች ለልብ ህመም ሊጋለጥ እንደሚችል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የአዋቂ የልብ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት ዶክተር ብርሃኑ ሞገስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የልብ ህመም ከተወሳሰብ ዘላቂ የጤና እክል እስከ ድንገተኛ ኅልፈት ያደርሳል። ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች ሰዎች ማሻሻል በሚችሏቸው (ሞዲፋይብል) እና ማሻሻል በማይችሏቸው (ነን ሞዲፋይብል ወይም ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች) ለልብ ህመም ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዶክተር ብርሃኑ ይገልጻሉ። መሻሻል ከሚችሉ አጋላጭ ምክንያቶች መካከል፤ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም (በአግባቡ መድኃኒቱ ካልተወሰደ)፣ተገቢ ያልሆነ የስብ ክምችት፣ ከፍተኛ ውፍረት (ክብደት)፣ በቂ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ አመጋገብ አለመኖር እንዲሁም አብዝቶ ስኳር፣ ጣፋጭና አልኮል መጠቀም የሚሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ እንዲሁም ሰዎች ማሻሻል ከማይችሏቸው (ተፈጥሯዊ) አጋላጮች መካከል፤ በቤተሰብ የሚተላለፍ መኖሩን፣ በዕድሜ መጨመር የሚከሰት መሆኑን (ለምሳሌ፡- ወንድ ከ45 ሴት ከ55 ዓመት በላይ ሲሆናቸው ለልብ ህመም ሊጋለጡ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩን) እንዲሁም ወንዶ ከሴቶች በይበልጥ ለልብ ህመም ተጋላጭ የመሆናቸው አጋጣሚ ሰፊ ሊሆን እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም የልብ ህመም ምልክቶች የደረት ውጋት በግራ በኩል ወይም መሐል ላይ፣ ከወትሮው የተለየ ድካም፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ከመደበኛው የተለየ የልብ ምት መኖር፣ የሰውነት በተለይም እግር አካባቢ እብጠት፣ ራስን መሳት እና ሳል የልብና ተያያዥ ህመም ምልክት ሊሆኑ እንደሚችሉ አብራርተዋል። የልብን ጤናን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ጤናማ አመጋገብን መከተል እንደሚገባ የሚመክሩት ዶክተር ብርሃኑ፤ አትክልት ማዘውተር፣ ምግብ ሲዘጋጅም ፈሳሽ ዘይት መጠቀም፣ ስኳር፣ ጨው እና ጣፋጭ ነገሮችን መገደብ ከተቻለም ማስወገድ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ ማዘውተር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ይህም ብስክሌት መንዳት፣ በእግር እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ዋና መዋኘት፣ እስከሚያልብ እና የልብ ምት እስከሚጨምር ብሎም እስከሚደክሙ የአካል ብቃት መሥራት የልብን ጤና ለመጠበቅ አስተዋጽዖ አለው ነው ያሉት፡፡ ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ማድረግ ተገቢ መሆኑን ያነሱት የሕክምና ባለሙያው፤ “ቦዲ ማስ ኢንዴክስ (ቢ ኤም አይ)” ከ18 ነጥብ 5 እስከ 25 እንዲሆን ይመከራል ብለዋል፡፡ ሲጋራ አለማጨስ፣ አልኮል አለመጠቀም፣ የስኳር ህመምና ከፍተኛ ደም ግፊት ካለም የመድኃኒት አወሳሰድን አለማስተጓጎል፣ አመጋገብ ላይ ስብ አለማብዛትና አብዝቶ አለመቀመጥ የልብ ህመምን ለመከላከል እንደሚያግዙ ነው ያስረዱት፡፡ ዕድሜያቸው ከ45 ዓመት በታች የሆኑ ጤናማ ሰዎች ከአንድ እስከ ሦስት ዓመት ባሉ ጊዜያት አንድ ጊዜ፣ ዕድሜያቸው ከ45 በላይ የሆኑ በየዓመቱ እንዲሁም የልብ ህመም ያለባቸው እንደሁኔታው በየጊዜው ክትትል እንዲያደርጉም መክረዋል፡፡ ሰዎች ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳቸውን ከልብ ህመም እንዲጠብቁ መክረው፤ ከዚህ ያለፈ ችግር ሲኖር ቶሎ የሕክምና ክትትል ማድረግ እና “ዛሬ ነገ” በማለት ጊዜ እያባከኑ ህመሙ ውስብስብ ደረጃ እስኪደርስ መጠበቅ እንደማይገባቸው አሳስበዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ጤና #የልብ_ህመም
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 1895
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 16224
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 9307
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 15070
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳው ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም
Jun 5, 2026 12557
የጤና ነገር በዮሐንስ ደርበው እንደዋዛ የበርካቶችን በር የሚያንኳኳውን ዲጂታል (ቨርቹዋል) ኦቲዝም እንዴት መከላከል ይቻላል? አንድ ሰው ኦቲዝም አለበት የሚባለው ምን ዓይነት ምልክቶች ሲታዩበት ነው? ከቨርቹዋል ኦቲዝም መንስዔ፣ ምልክቶቹ፣ የሚያስከትለው ጉዳትና ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ መንክር ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል። መነሻ ልጆች በአራት የዕድገት ዘርፎች እንደሚያድጉ ያነሱት ወ/ሮ መዓዛ፤ እነሱም የቋንቋ ክኅሎት ዕድገት፣ የአዕምሮ (ነገሮችን፣ ሁኔታዎችን) የመረዳት ዕድገት፣ አካላዊ ዕድገት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕድገት መሆናቸውን ያብራራሉ። በዚህም መሠረት ይላሉ ባለሙያዋ፤ አንድ ልጅ ጤናማ ወይም ሙሉ ዕድገት አለው የሚባለው በአራቱም የዕድገት ደረጃዎች በተመጣጠነ ሁኔታ ሲያድግ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት። ምንድንነት? ባለሙያዋ ኦቲዝም በሁለት ተከፍሎ እንደሚታይ ጠቁመው፤ የመጀመሪያው ከመጀመሪያ ጀምሮ በሕክምና የተረጋገጠ በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች ወይም “ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር” (ዋናው ኦቲዝም) እንደሚባል ይገልጻሉ። ሁለተኛው ቨርቹዋል ኦቲዝም መሆኑን ገልጸው፤ ይህ ማለት ደግሞ ኦቲዝም የሚመስል ምልክቶች የሚያሳዩ ልጆችን የሚገልጽ እንጅ፤ ዋናው ኦቲዝም እንዳልሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይላሉ ወ/ሮ መዓዛ፤ አንድ ልጅ ከላይ ከተገለጹት ከአራቱ ሁለቱ በተለይም የቋንቋ ክኅሎት እና የማኅበራዊ መሥተጋብርና የተግባቦት ዕክል ሲገጥመው፤ ዋናው ኦቲዝም አለበት እንደሚባል አስገንዝበዋል። የጡት ካንሰርን ለመከላከል ለልብ ህመም አጋላጭ መንስዔዎች በወቅቱ ካልታከመ ለኩላሊት መድከም፣ ለደም መመረዝና ለሞት የሚያደርሰው በዓለም ላይ አሳሳቢ ደረጃ ከደረሱ የህመም ዓይነቶች አንዱ ለቨርቹዋል ኦቲዝም አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ዓመት ባለው ዕድሜያቸው ለተንቃቃሽ ስልኮች፣ ታብሌቶች፣ ቴሌቪዥን (ለስክሪኖች) ለረጅም ሠዓታት በድግግሞሽ ተጋላጭ ሲሆኑ ለኦቲዝም መሰል ምልክቶች (ቨርቹዋል ኢቲዝም) ተጋለጡ ተብሎ እንደሚወሰድ የአእምሮ ሕክምና ባለሙያዋ ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም ልጆች ከሰዎች ጋር ባለመቀራረብ፣ በገሃዱ ዓለም የሚደረገውን ነገር ካላማየት የተነሳ ያልተለመዱ (አዳዲስ) ባሕርያትን እንደሚያዳብሩ ጠቁመው፤ እነዚህ ባሕርያትም ኦቲዝም መሰል (ቨርቹዋል ኦቲዝም) መሆናቸውን ይገልጻሉ። ጉዳዩን በምሳሌ ሲያብራሩም፤ ከዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ተግባብቶ መጫወት ምን እንደሆነ አለማወቅ፣ ተረጋግቶ መቀመጥ አለመቻል፣ በገሃዱ ዓለም ለሚደረጉ ነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የእንቅልፍ መዛባት፣ ለስክሪን እና ዲጂታል ለሆኑ ነገሮች ሱሰኛ መሆን (ምግብ ሲበሉ ሞባይል መያዝ፣ ቴሌቪዥን ዕያዩ መብላት መፈለግ)፣ ማንኛውንም ነገር ሞባይል ወይም ቴሌቪዥን ካልተከፈተ ማድረግ አለመቻል (አለመፈለግ) የሚሉት የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን ነው የዘረዘሩት። ይህን ተከትሎም ይላሉ ባለሙያዋ፤ የቋንቋ ክኅሎታቸው እንደ ዕድሜ እኩዮቻቸው የዳበረ አይሆንም፤ ከዚህም ሲያልፍ ኦቲዝም መሰል ምልክቶች በሚኖሩበት ወቅት በቀላሉ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመግባባት በጣም ይቸገራሉ ሲሉ አስገንዝበዋል። የኦቲዝም መንስዔ ምንድን ነው? እንዴት መጣ? የሚለው እስካሁን በመጠናት ላይ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዋ፤ ቨርቹዋል ኦቲዝም ግን መንስዔው እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል። መንስዔውም ልጆች ለረጅም ሠዓትና በድግግሞሽ (ለብዙ ጊዜያት) ለስክሪን ተጋላጭ መሆናቸው ነው ይላሉ። ልጆች ቴክኖሎጂን መቼ ይጠቀሙ? እንደ ባለሙያዋ ገለጻ፤ ልጆች ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት በፍጹም እንዳይጠቀሙ ይመከራል። በአንጻሩ ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያወሩ፣ አካባቢያቸውን እንዲያዩ፣ በመንቀሳቀስና በመነካካት ገሃዱን ዓለም እንዲረዱ እንደሚመከር አመላክተዋል። ቴክኖሎጂን መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከሁለት እስከ ስድስት ዓመታቸው፤ ቋንቋን (ንግግርን) የሚያበረታቱ፣ ትምህርት ሰጭ ሆነው ከተገኙ ከአዋቂዎች ጋር በመሆን የጨዋታ ክኅሎትን የሚያዳብሩ ንግግር ያላቸው (መዝሙሮችና ሌሎችንም) በቀን ለ30 ደቂቃ እንዲመለከቱ ማድረግ ይመከራል ብለዋል። ንግግር የሌላቸው ቪዲዮዎች ግን ልጆች ከፊልሙ ዐይተው እንኳን ቋንቋ እንዳይማሩ ስለሚገድቡ ለልጆች ተገቢ አይደሉም ይላሉ። ከሁለት እስከ ስድስት ዓመት ለሆናቸው ግን ትምህርታዊ ጉዳይ ከሆነ እና ልጄ ስነግረው ስላልገባው በስክሪን ሳሳው ሊገባው ይችላል ብለው ወላጆች ሲያስቡ ለዚያውም ከአዋቂዎች ጋር በመሆን ለማስተማር ብቻ እስከ 30 ደቂቃ በቀን መጠቀም ቢችሉ ጥሩ ነው ብለዋል። እነማን ተጋላጭ ናቸው? ብዙ ጊዜ ወላጆች ባለማወቅ ልጆች ሲንቀሳቀሱ፣ ያገኙትን ሲነካኩ ጥፋት ይከሰታል፣ ይወድቃሉ … በሚል እሳቤ አርፈው እንዲቀመጡ በማሰብ ስልክ ይሰጧቸዋል፤ ቴሌቪዥንም ይከፍቱላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ መዓዛ፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሉ ልጆች ተጋላች መሆናቸውን አንስተዋል። ስለዚህ ወላጆች ለረጂም ሠዓት እና በተደጋጋሚ ጊዜ ታብሌት፣ ስልክ እና ቴሌቪዥን ለልጆች መክፈት ለቨርቹዋል ኦቲዝም እንደሚያጋልጥ ተገንዝበው፤ የልጆቻቸውን ጤና ከማወክ ቢቆጠቡ መልካም መሆኑን አመላክተዋል። ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መጠቃታቸውን ማወቅ ይቻላል? እንደ ወ/ሮ መዓዛ ማብራሪያ፤ ልጆች በቨርቹዋል ኦቲዝም መያዛቸውን ወላጆችም በቤታቸው ማወቅ ይችላሉ፤ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድም በምርመራ ማወቅ ይቻላል። ወላጆች በቤት ውስጥ መለየት የሚችሉበት ስልትም፤ ቴሌቪዥን ሲጠፋ፣ ሞባይል ሲከለከሉ ልጆች በከፍተኛ ሁኔታ የሚበሳጩ ከሆነ፣ ምግብ አልበላም የሚሉ ከሆነ፤ አልታዘዘም ካሉ፣ ተረጋግተው የማይቀመጡ ከሆነ፣ እየተንቀሳቀሱ ቁጣቸውን የሚገልጹ ከሆነ እነዚህ ምልክቶች ሱስ እንደሆነባቸው ይጠቁማል ይላሉ። በተጨማሪም የንግግር መዘግየት ካለ፣በአካባቢያቸው ስለሚከናወኑ ሁኔታዎች ብዙም ትኩረት የማይሰጡ ከሆነ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች መሆናቸውን በመግለጽ፤ ለተሻለ የባለሙያ እገዛ በዚህ ጊዜ ልጆችን ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ እንደሚገባ ይመክራሉ። ሕክምና ቀዳሚው የሕክምና አካል የኦቲዝሙን ዓይነት በምርመራ መለየት መሆኑን ወ/ሮ መዓዛ አስረድተዋል።ይህም ማለት በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች (ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ነው ወይስ ቨርቹዋል ኦቲዝም ነው የሚለው ከተለየ በኋላ ወደ ቀጣዩ ሂደት መሄድ ይገባል ይላሉ። በዚህም መሠረት፤ ልጆ ከስክሪን (ቴሌቪዥን፣ ሞባይል፣ ታብሌት…) እንዲከለከሉ ማድረግ የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያመላከቱት። በተጨማሪም ከቤት ወጥተው ከልጆች ጋር እንዲጫወቱ ብሎም የገሃዱን ዓለም እንቅስቃሴ፣ የአኗኗር ሁኔታ እንዲያዩ እና እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። የቋንቋ (ንግግር) መዘግየቱ ከባድ ከሆነ (ከእኩዮቻቸው በጣም ወደ ኋላ የቀሩ ከሆነ) ደግሞ ልጆቹ “ስፒች ቴራፒ” እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል። አክለውም ወላጆች ልጆችን ወደ ቤተሰብ እንዲሁም ወደ መዝናኛ ስፍራ ይዘዋቸው በመሄድ ከሰዎች ጋር ያላቸውን መቀራረብ እንዲያሳድጉ ትኩረትና ጊዜያቸውን ለልጆች መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ወ/ሮ መዓዛ እንዳሉት፤ ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ተደርገው መሻሻል ከሌለ (ልጆቹ ካልተሻላቸው) ዋናው ኦቲዝም (በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆች/ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር) ሊሆን ይችላል ብለዋል። ስለዚህ ለዚህኛው የሚሆነውን የሕክምና ክትትል በባለሙያ ታግዘው ማከናወን ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። በአጠቃላይ ግን የኦቲዝም ሕክምና ባብዛኛው ከመድኃኒት ይልቅ በትምህርታዊ ሥልጠና በመታገዝ የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የሚድንበትን ጊዜ ማወቅ እንደማቻል አመላክተዋል። በእርግጥ መድኃኒት የሚታዘዝበት ጊዜም እንዳለ ጠቁመው፤ ይህም ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ ማጣት ካለ፣ ቤተሰብን የመረበሽ ነገር ካለ፣ ከፍተኛ የሆነ አስቸጋሪ ባሕርይ ሲኖር በባለሙያ ታይቶ ነው ብለዋል። ምክረ ሐሳብ ለቴክኖሎጂ ተጋላጭ መሆን ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፤ ለአጠቃቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለይም በከተሞች አካባቢ ልጆች እንዳይረብሹ በሚል ሞባይል፣ ቴሌቪዥን፣ ታብሌትን እንደ ሞግዚት የመጠቀም ልማድ መኖሩን አንስተዋል። ይህም በልጆች ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል ወላጆች (ሠራተኞች፣ ሞግዚቶች) መገንዘብ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። ምንም እንኳን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት ባይኖርም፤ ከዲጂታል አማራጭና አቅርቦት አኳያ በከተሞች ለቨርቹዋል ኦቲዝም የመጋለጥ ሁኔታው ሰፊ እንደሆነ ይታመናል ሲሉም አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #የጤና_ነገር #ኦቲዝም #ቨርቹዋል
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 8133
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !