ጃዋር መሀመድ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ - ኢዜአ አማርኛ
ጃዋር መሀመድ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ ሰኔ 29/2010 የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) መስራች እና ፖለቲካ አክቲቪስት የሆነው ጃዋር መሀመድ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ከጃዋር በተጨማሪ ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋዲሳ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ገብተዋል። የኦህዴድ የጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አደርገውለቸዋል። ጃዋር ከዛሬ 13 አመት በፊት በትምህርት ምክንያት አገሩን ለቆ ወደ አሜሪካ መወጣቱ ይታወቃል። በአሜሪካን አገር በነበረው ቆይታ የፖለቲካ አክቲቪስት ሆኖ በአገር ጉዳይ ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሲንቀሳቀስ እንደነበር ይታወቃል ። በዚህ የፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት በኢትዮጵያ መንግስት ክስ ተመስርቶበት እንደነበር ይታወሳል። OMN እና ጃዋር መሀመድ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ በቅርብ ጊዜ በተደረገው ይቅርታ ተነስቷል። በመሆኑም ጃዋር አገር ውስጥ ሆኖ ለመስራት ወደ አገር ቤት ተመልሷል። በተጨማሪ የፖለቲካ ምሁር የሆኑት ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ጋዲሳና ሌሎች ኢትዮጵያውያኖች አብረው ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል።