የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 116ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በስፖርታዊ ውድድሮች እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 116ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እያከበረ ነው።

በስፖርታዊ ዉድድሩ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት የፌደራል ፖሊስ ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያን ስፖርት በመገንባት ረገድ ስሙ በጉልህ የሚነሳ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ከፍ ካደረጉ አንጋፋ ስፖርተኞች መካከል ከፌደራል ፖሊስ ስፖርት ክለብ የተገኙ ስፖርተኞች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

በቀጣይም የፖሊስ መደበኛ ተግባር ከሆነው ወንጀልን መከላከል በተጨማሪ ለአገሪቱ የስፖርት እድገት የበኩሉን ድርሻ የሚወጣ ይሆናል ብለዋል።


 

እግር ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ አትሌቲክስ፣ ጠረፔዛ ቴንስና ገመድ ጉተታ ውድድር የሚካሄድባቸው የስፖርት አይነቶች ናቸው።

ስፖርታዊ ውድድሮቹ ከዛሬ ጀምሮ  እስከ ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆዩ መሆኑ ተመላክቷል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም