የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅን አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅን አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ ታኅሳስ 22/2017(ኢዜአ)፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን አጸድቋል።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አጽድቋል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ታደለ ቡራቃ(ዶ/ር) በአዋጁ የተጨመሩ ድንጋጌዎች፣ ማሻሻያ የተደረገባቸውንና አስፈላጊነቱን አስመልክተው የረቂቅ አዋጁን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል።
አዋጁ የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነትን፣ ተደራሽነትና ጥራትን እንዲሁም የህዝብ ጥቅም፣ ባህልና ሃይማኖትን በጥንቃቄና በጥልቀት በመመልከት የተዘጋጀ መሆኑን የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።
ምክር ቤቱ የተሰጡ አስተያየቶችን በማከል አዋጁን በአንድ ተቃውሞ በዘጠኝ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።