በክልሉ ከ7ሺህ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል - የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ ከ7ሺህ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል - የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ከ7ሺህ 3 መቶ በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የሀረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገለፁ።
የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም የኮደርስ ስልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር እንደሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ እንደሚያግዝ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተሰራው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 3ሺህ የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ጠቁመዋል።
በመርሀ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙም መግለጻቸውን ከክለሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ማፍራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።
ስልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል በሆኑ ስልጠናውን ያልወሰዱ በቀጣይ ግዜያት እንዲመዘገቡ እና እንዲሰለጥኑ ሀላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ9ሺህ በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም አቶ ጀማል ኢብራሂም ገልጸዋል። https://ethiocoders.et/