ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሃኖይ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ):-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሃኖይ እየተገነባ የሚገኘውን ትልቅ የዘመነ ከተማ (የስማርት ሲቲ) ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

ይኽም ለኢትዮጵያ የከተማ ልማት ሥራ የሚሆን ተሞክሮ የመቅሰም ተግባር አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።


 

ጉብኝቱ ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የዘመናዊ ከተማ ፕሮጀክቶችን ለማላቅ የሚደረግ ፍላጎትና ጥረትን እንደሚያሳይ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም