ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተከናውነዋል-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - ኢዜአ አማርኛ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተከናውነዋል-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 9/2017 (ኢዜአ)፡-በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች መከናወናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ ዋና ዋና የዲፕሎማሲ ስራዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ለጎረቤት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በዚህም ከጎረቤት ሀገር ጋር ያላትን ትስስር የሚያጠናክሩ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
በየካቲት ወር የተካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በልዩ አድናቆት የታየ እንደነበር አመላክተዋል።
በህዝብ ለህዝብ ግንኙነትም ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጸው፥ ለአብነትም 968 የሚሆን ነጻ ከፍተኛ የትምህርት እድል ማመቻቸት መቻሉን ጠቁመዋል።
ከተለያዩ አገራት ጋር የሚደረጉ ስምምነቶች ጋር በተያያዘም 11 ስምምነቶች ለምክር ቤት ቀርበው መጽደቃቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አቅምን በማሳደግ ተጽእኖ ፈጣሪነቷ እንዲጎለብት ማስቻሉን ገልጸዋል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ስራዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ 92 ሺህ በላይ ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል።