በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ተጀመረ

መቀሌ፤ ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ)፦በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ዳግም ተጀምሯል።

የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ተቋማት ታዛቢዎችና ተወካዮች ለቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች የሚሰጠውን የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም የስልጠና ሂደት ተመልክተዋል።


 

በምልከታው ላይ የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ፍስሀ ኪዳኑ፣ በአፍሪካ ሕብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የቁጥጥር፣ ማረጋገጥና ማስከበር ተልዕኮ ልዑክ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ሳማድ አላዴ፣ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የአጋር የልማት ድርጅቶችና የሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለቀድሞ ታጣቂዎች የሚሰጠው የተሀድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ተቋርጦ ቆይቷል።

በመሆኑም የቀድሞ ታጣቂዎችን የማረጋገጥ፥ ዲሞቢላይዝ የማድረግ፥ የመመዝገብና የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ዳግም ዛሬ በመቀሌ የተሃድሶ እና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ማዕከል ተጀምሯል።

በክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን የዲሞብላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም