ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፦ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት(UNOPS) የኢትዮጵያ መንግስት በሚያከናውናቸው በተለያዩ የግዢ ሂደቶች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡


 

የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤቱ በአፍሪካ ውስጥ በሚያከናውናቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያውያን ዕቃ አቅራቢዎችን እንዲያሳትፍና ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ጽህፈት ቤት እንዲያስፋፋም መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ በበኩላቸው ከፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡


 

ጽሕፈት ቤቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም