አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የጅቡቲ ብሄራዊ የሜዳሊያ ሽልማት አገኙ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የጅቡቲ ብሄራዊ የሜዳሊያ ሽልማት አገኙ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2017 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የጅቡቲ ብሄራዊ የሜዳሊያ ሽልማት ዛሬ ተበርክቶላቸዋል።
አምባሳደር ብርሃኑ ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ብዱልቃድር ካሚል መሀመድ የ “ጁን27 ኦፊሰር ዳንስ ላሬድ ናሽናል ሜዳሊያ” በመቀበሌ እጅግ ደስ ብሎኛል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በየደረጃው ይበልጥ እንዲጠናክር ላሳዩት ቤተሰባዊ ድጋፍ እና ክትትል ልዩ ምስጋዬን ላቀርብ እወዳለሁ ብለዋል።
ጅቡቲ ሁለተኛ አገሬ ናት ያሉት አምባሳደሩ የኢትዮጵያና የጅቡቲ ግንኙነት በጋራ ህዝቦች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ወዳጅነት እና የዘመናት ወንድማማችነት ያለን ህዝቦች ነን ሲሉ ገልጸዋል።
ለቀጣናው ተምሳሌት የሆነው የሀገራቱ የኢኮኖሚ ትስስር በአህጉራዊ እና አፍሪካዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው እንደሚቀጥል አመልክተዋል።
አምባሳደር ብርሃኑ የጅቡቲ መንግስት በቆይታቸው ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።