የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ 4ተኛ አመት 10 መደበኛ ስብሰባውን 3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

አጀንዳዎቹም

1. ተቋርጦ የነበረው የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።

2. የብርሃን አይነ ሰውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ምህርት ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማው ትምህርት ቢሮ እንዲሆን  የቀረበውን ደንብ መርምሮ አጽድቋል ::

3. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ ማጽደቁን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም