የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሃ ግብር 

አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 11/2017 (ኢዜአ)፡-  የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል። 

ኤቨርተን ከማንችስተር ሲቲ ከቀኑ 11 ሰዓት፣ አስቶንቪላ ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

ጨዋታዎቹ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ጠንካራ ፉክክር እያደረጉ ለሚገኙት ማንችስተር ሲቲ፣ አስቶንቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ወሳኝ የሚባሉ ናቸው። 

በሌሎች መርሃ ግብሮች ብሬንትፎርድ ከብራይተን፣ ዌስትሃም ከሳውዝሃምፕተን  እና ክሪስታል ፓላስ ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ነገ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከሌይስተር ሲቲ እንዲሁም ተከታዩ አርሰናል ከኢፕስዊች ታውን  ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም