የሐረሪ ክልል ምክር ቤት እና የጣሊያን ካላብሪያ ክልል ምክር ቤት የልምምድ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2017(ኢዜአ)፡- የሐረሪ ክልል ምክር ቤት እና የጣልያን ካላብሪያ ክልል ምክር ቤት የልምምድ ልውውጥ አድርገዋል።

በጣልያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው ሁነት ላይ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ሱልጣን አብዱልሰላም የተመራ ልዑክ ከካላብሪያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ፊሊፖ ማንኩሶ(ዶ/ር) ልዑክ ጋር ተወያይቷል።

በካላብሪያ ክልል በብዝሃ ቋንቋ አጠቃቀም ረገድ ያለውን የህግ ማዕቀፍና አተገባበርን በተመለከተ የክልሉ ተሞክሮዎች ላይ ምክክር ተደርጓል።

ሁለቱ ክልሎች በተለያዩ ዘርፎች በትብብር ለመስራትም ተስማምተዋል።

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ የካላቢሪያ ክልል ምክር ቤትን እንዲሁም የተለያዩ ቅርሶችንና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ጎብኝቷል።

ልዑኩ በጣልያን የስራ ጉብኝት እያደረገ እንደሚገኝ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም