ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 12/2017 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንችስተር ሲቲ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በጉዲሰን ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ ኒኮ ኦለራይሊ እና ማቲዎ ኮቫቺች የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ58 ነጥብ ደረጃውን ከ5ኛ ወደ 4ኛ ከፍ አድርጓል። በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ጉዞ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
ኤቨርተን በ38 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌሎች ጨዋታዎች ብሬንትፎርድ ብራይተንን 4 ለ 2 አሸንፏል።
ዌስትሃም ዩናይትድ ከሳውዝሃምፕተን አንድ ለአንድ፣ ክሪስታል ፓላስ ከቦርንማውዝ ዜሮ ለዜሮ በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ በቪላ ፓርክ ስታዲየም አስቶንቪላ ከኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።