የሊጉ መሪ ባርሴሎና ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 11/2017 (ኢዜአ):- በስፔን ላሊጋ የ32ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባርሴሎና ሴልታቪጎን 4 ለ 3 አሸንፏል። 

ማምሻውን በካምፕኑ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ራፊኒያ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ዳኒ ኦልሞ እና ፌራን ቶሬስ ቀሪዎቹን ግቦች ለባርሴሎና አስቆጥረዋል። 

ለሴልታቪጎ ቦርጃ ኢግሌሲያስ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል። 

ባርሴሎና 3 ለ 1 እየተመራ ጨዋታውን የቀለበሰበት መንገድ አድናቆት አስችሮታል።

ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና በ73 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል። ከተከታዩ ሪያል ማድሪድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ከፍ አድርጓል።

ሪያል ማድሪድ ከአትሌቲኮ ቢልባኦ ነገ ጨዋታውን ያደርጋል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም