አስቶንቪላ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል 

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 12/2017 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ አስቶንቪላ ኒውካስትል ዩናይትድን 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። 

ማምሻውን በቪላ ፓርክ በተካሄደው ጨዋታ ኦሊ ዋትኪንስ፣ ኢያን ማትሰን፣ አማዱ ኦናና እና የኒውካስትል ዩናይትዱ ተከላካይ ዳን ባርን በራሱ ግብ ላይ ለቡድኑ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። 

ፋቢያን ሻር ለኒውካስትል ዩናይትድ የማስተዛዘኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ አስቶንቪላ በ57 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። 

ኒውካስትል ዩናይትድ በ59 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል። 

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ተሳትፎ ለማግኘት እየተደረገ ያለው ጠንካራ ፉክክር ይበልጥ አጓጊ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም