ቅዱስ ጊዮርጊስ ከስምንት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 11/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 1 አሸንፏል። 

ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢኒያም ፍቅሩ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር አብዱ ሳሚዮ ቀሪዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ቡልቻ ሹራ ለወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል። 

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ34 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። ከስምንት ጨዋታዎች በኋላም ወደ አሸናፊነት ተመልሷል። 

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ11 ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃ ይዟል።

ቀን ላይ በተደረገ የ26ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን  3 ለ 1 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም