የኢትዮዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ቀን ውሎ

አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 12/2017 (ኢዜአ)፡-  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት  ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ ቡና በ39 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ሲዳማ ቡና በ32 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቡናማዎቹ ካሸነፉ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያላቸውን ልዩነት ወደ ስድስት ዝቅ ያደርጋሉ።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከስሑል ሽሬ ይጫወታሉ።

አርባምንጭ ከተማ በ34 ነጥብ 8ኛ ደረጃን ይዟል። ስሑል ሽሬ በ17 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። 

በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን በተመሳሳይ 3 ለ 1  አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም