ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 12/2017 (ኢዜአ):-  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ 0 አሸንፏል። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን በ13ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሏን ከመረብ ላይ አሳርፏል። 

ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ 9ኛ ድሉን አሳክቷል።  

በአንጻሩ በሊጉ 7ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በ39 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

ምሽት 12 ሰዓት ላይ አርባምንጭ ከተማ ከስሑል ሽሬ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም