አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 12/2017 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታ አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በፖርትማን ሮድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሊያንድሮ ትሮሳርድ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ኢታን ንዋኔሪ ቀሪዎቹን ጎል ለመድፈኞቹ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
የኢፕስዊች ታውኑ ተከላካይ ሌፍ ዴቪስ በ32ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ነጥቡን ወደ 66 ከፍ አድርጓል። ከሊጉ መሪ ጋር ያለውን ልዩነት በጊዜያዊነት ወደ 10 ዝቅ አድርጓል።
ኢፕስዊች ታውን በ21 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በሌሎች ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው በዎልቭስ የ1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል።
ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ከመመራት ተነስቶ ፉልሃምን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ሌይስተር ሲቲ የሊጉን መሪ ሊቨርፑል ያስተናግዳል።