አርባምንጭ ከተማ እና ስሑል ሽሬ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 12 /2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 26ኛ ሳምንት አርባምንጭ ከተማ እና ስሑል ሽሬ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ጨዋታው ማምሻውን በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል።

ውጤቱን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ በ35 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

ስሑል ሽሬ በ18 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

ቀን ላይ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም