በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ ፤ሚያዚያ 13/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ሶስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
የመጀመሪያው ጨዋታ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከ30 በአዳማ ከተማ እና መቻል መካከል በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይከናወናል።
አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። መቻል በ35 ነጥብ 6ኛ ደረጃን ይዟል።
ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ ይጫወታሉ።
ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ሲይዝ ድሬዳዋ ከተማ በ26 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የዕለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ እና መቀሌ 70 እንደርታን ያገናኛል።
ባህር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል። መቀሌ 70 እንደርታ በ28 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ የ26ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ አርባምንጭ ከተማ እና ስሑል ሽሬ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል።