መቻል ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 13/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ረፋድ ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል በ38 ነጥብ ደረጃውን ከ6ኛ ወደ 3ኛ ከፍ ያደረገ ሲሆን በሊጉ 10ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከሰዓት በኋላ ቀጥሎ ሲውል ፋሲል ከነማ ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ባህር ዳር ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።