የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ - ኢዜአ አማርኛ
የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ)፦ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተገልጿል።
ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች።