ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፖፕ ፍራንሲስ የርህራሄ፣ የመልካም እና የአገልግሎት ዘመን አሻራ ትውልዶችን እያነሳሳ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ መልዕክት።