ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ-ሕይዎት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ-ሕይዎት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ)፦ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ-ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ታዬ በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ሙሉ የህይወት ዘመናቸውን ለዓለም ሰላም ሲሰሩ በቆዩት በሊቀ ጳጳሱ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል።