ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ-ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ።

ብፁዕነታቸው ለመላው የሮማ ካቶሊካዊ መሪዎች እና በመላው ዓለም ላሉ ምዕመናን እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም