የሰላም ሚኒስቴር በብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የሰላም ሚኒስቴር በብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017 (ኢዜአ):- የሰላም ሚኒስቴር በሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ በብጹዕ ወቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ኅልፈት ከፍተኛ ሀዘን ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ምእመናን መጽናናትን እንደሚመኝ በሀዘን መግለጫው አመልክቷል።