ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ):- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አስራት ቶንጆ በ54ኛው ደቂቃ የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በ29 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱም ስድስተኛ ድሉን አሳክቷል።
በአንጻሩ በሊጉ 7ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ ይጫወታሉ።