ኖቲንግሃም ፎረስት ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 13/2017(ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በለንደን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤሊዮት አንደርሰን እና ክሪስ ውድ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሪቻርልሰን ለቶተንሃም ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

ድሉን ተከትሎ ኖቲንግሃም ፎረስት በ60 ነጥብ ደረጃውን ከ5ኛ ወደ 3ኛ ከፍ አድርጓል።

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የተሳትፎ ህልሙን ለማሳካት በሚያደርገው ጉዞ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ጠንካራ ፉክክር ይበልጥ አጓጊ ሆኗል።

በተያያዘም ዛሬ በእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ የተደረጉ ጨዋታዎችን ተከትሎ ሊድስ ዩዩናይትድ እና በርንሌይ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም