በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም መስክ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ልማቶች ተከናውነዋል

ሐረር፤  ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ)፡-  በሐረሪ ክልል ባለፉት ዘጠኝ  ወራት በሁሉም መስክ የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የክልሉ የአስፈፃሚ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፎች የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው።


 

የግምገማውን መድረክ እየመሩ የሚገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የገጠርና የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ልማቶች ተከናውነዋል።

በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሃብት እና በመልካም አስተዳደር  መስኮች የተከናወኑ ስራዎች የክልሉን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ሃብቶች በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማስቻሉን በመጥቀስ።

እነዚህን ውጤቶች ይበልጥ ለማስቀጠል የግምገማው መድረክ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም በግምገማው የተንጠባጠቡ ስራዎችና ክፍተቶች ተለይተው እስከ ሰኔ 30 ድረስ በተቀናጀ መንገድ ለማጠናቀቅ መደላድል ይፈጠራል  ብለዋል።


 

በግምግማው መድረክ ላይ የክልሉ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኢብሳ ኢብራሂም የዘጠኝ ወራት  የካፒታል ፕሮጀክቶች  የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ግምገማ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የየወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም