የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ ፤ ሚያዚያ 14/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ጨዋታውን ያካሂዳል። 

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል። 

ኢትዮጵያ መድን በ48 ነጥብ የአንደኝነት ደረጃውን ተቆናጧል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ29 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዟል።

መድን ካሸነፈ ከተከታዩ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 11 ከፍ ያደርጋል። 

ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ስፍራ ለመራቅ ያስችለዋል። 

የ26ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ምሽት 12 ሰዓት ላይ ያገናኛል።

ሃዋሳ ከተማ በ24 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

በተያያዘም ትናንት በተካሄዱ የ26ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ጨዋታዎች ባህር ዳር ከተማ መቀሌ 70 እንደርታ 4 ለ 1 ፣ መቻል አዳማ ከተማን 2 ለ 0 እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም