119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን “የድል ሰራዊት” በሚል መሪ ሀሳብ በመከበር ላይ ነው።
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በመርሀ ግብሩ ላይ በመከላከያ ሙዚየምና ቅርስ ጥናት አስተዳደር የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን መርቀው ከፍተዋል።
በዚህ መርሀ-ግብር ኢታማዦር ሹሙን ጨምሮ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የመከላከያ ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የቀድሞ የሠራዊቱ አመራሮች፣ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የሠራዊት ቀን የመከላከያ ሰራዊት በዘመናዊ መልኩ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የተመሰረተበትን ታሪክ በማሰብ ይከበራል።
በዓሉ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሚኒስትር የሰየመችበትን ቀን በማስታወስ ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ይዘከሩበታል።
የበዓሉ ዓላማም የሰራዊቱን ጀግንነት፣ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሚና እና ታላቅ አኩሪ ታሪክ ለትውልድ በቅብብሎሽ ማስተላለፍ ነው።