ቀጥታ፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ህልውና ምሶሶ ነው - ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ህልውና ምሶሶ ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ።

ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋ ቀይ ባህርም ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ያበጀው ባህር መሆኑን ገልጸዋል።

119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን የድል ሰራዊት በሚል መሪ ሀሳብ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል።


 

ቀኑ የመከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ መልኩ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የተመሰረተበትን ታሪክ በማሰብ ይከበራል።

ይህም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሚኒስትር የሰየመችበትን ቀን በማስታወስ ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ይዘከሩበታል።

ዓላማውም የሠራዊቱን ጀግንነት፣ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሚና እና ታላቅ አኩሪ ታሪክ ለትውልድ በቅብብሎሽ ማስተላለፍ ነው።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ዕድሜ ጠገብ ተቋማት ከገነቡ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

119 ዓመት ያስቆጠረው መከላከያ ቀዳሚው አንጋፋው ተቋም መሆኑንም ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሀገር አፍራሽ ባንዳዎችን እየተዋጋ መሆኑን ገልጸው፤ ሠራዊቱ የሀገር ህልውና ምሶሶ መሆኑን ገልጸዋል።


 

መላላክ የተጠናወተው ሕወሓት በለኮሰው እሳት መለብለቡን ገልጸው፤ ወደ ወዳጁ ሻዕቢያ ሄዷል ድጋሚም ዕድል እንደሌለው ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋ ቀይ ባህርም ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ያበጀው ባህር ነው ብለዋል።

የሀገር መከላከያ የቀጣናው አስተማማኝ ሀይል መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ ሰራዊቱን በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የመከላከያ ሰራዊት የክብር አባልነት ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም